Mon Oct 03 2016 09:29:18 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
Getachew_Yohannes 2016-10-03 09:29:18 +03:00
commit fe231d32c9
60 changed files with 66 additions and 1 deletions

1
00/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
የዮሐንስ ራእይ

1
01/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 1 \v 1 \v 2 \v 3 1 ይህ ፈጥኖ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ራእይ ነው። እርሱም ይህን ራእይ መልአኩን ወደ አገልጋዩ ወደ ዮሐንስ በመላክ እንዲታወቅ አድርጓል። 2 ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል በሚመለከት ስላየው ማንኛውንም ነገር እና ክርስቶስን በሚመለከት ስለተሰጠው ምስክርነት ተናግሯል። 3 ዘመኑ ስለ ቀረበ ፥ የዚህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው፤እንዲሁም የሚሰሙት ሁሉ በውስጡም የተጻፈው ን ነገር የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።

1
01/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 \v 5 \v 6 4 ከዮሐንስ፥በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ካለው፥ከነበረው፥ወደፊትም ከሚመጣውና በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች 5 እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥ 6 አባቱ ለሆነው አምላክ መንግሥትና ካህናት እንሆን ዘንድ ላደረገን ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።

1
01/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 \v 8 7 እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን። 8 ጌታ አምላክም፥« አልፋና ኦሜጋ፥ ያለሁና የነበርሁ፥ወደፊትም የምመጣው ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ» ይላል።

1
01/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 \v 11 9 እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ። 10 በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ። 11 ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ከዚያም በኤፌሶን፥በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥በትያጥሮን፥በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።

1
01/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 \v 13 12 ይናገረኝ የነበረው የማን ድምፅ እንደ ሆነ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወር በምልበትም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ። 13 በመቅረዞቹም መካከል እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰና ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ የሰው ልጅ የሚመስለው ነበር።

1
01/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 \v 15 \v 16 14 ራሱና ጸጉሩ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር ማለትም እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ፤ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል፥ 15 እግሮቹም በእቶን እሳት እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፥ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውኃ ድምፅ ነበር። 16 በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ፊቱም ጸሐይ በሙሉ ኀይልዋ ስታበራ የምታበራውን ያህል ያበራ ነበር።

1
01/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 \v 18 17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ፤ እርሱም ቀኝ እጁን በእኔ ላይ በመጫን እንዲህ አለኝ፤«አትፍራ፤እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው 18 ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።

1
01/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
19 ስለዚህ ያየኽውን፥አሁን ያለውን ሁኔታና ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ነገር ጻፍ። 20 በቀኝ እጄ ያሉት አንተም ያየሃቸውን የሰባቱን ከዋክብትና የሰባቱን የወርቅ መቅረዞች ምስጢር በተመለከተ ትርጉሙ ይህ ነው፤ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ሲሆኑ፥ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

1
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 2 \v 1 \v 2 1 «በኤፌሶን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤<እነዚህ ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘው የእርሱ ቃሎች ናቸው። በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እርሱ እንዲህ ይላል፤2''' ሥራህን፥ልፋትህን እና በትዕግሥት መጽናትህን እንዲሁም ክፉ የሆኑትን ሰዎች እንዳልታገሥህ እና ሐዋርያት ሳይሆኑ ራሳቸውን ሐዋርያት አድርገው የሚቆጥሩትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ።

1
02/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 \v 4 \v 5 3 በትዕግሥት እንደ ጸናህ፥ስለ ስሜ ብዙ መከራ ቢደርስብህም እንዳልደከመህ አውቃለሁ። 4 ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ይኽውም የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃል። 5 እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ ለይተህ እወቅ፤ንስሓ ግባ፤ቀደም ሲል ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። ንስሓ ካልገባህ እመጣብሃለሁ፤መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ።

1
02/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 \v 7 6 ነገር ግን አንድ መልካም ነገር አለህ፤እኔ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሓልና። 7 ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ፤ድል ለሚነሳ በእግዚአብሔር ገነት ካለችው የሕይወት ዛፍ እንዲበላ እፈቅድለታለሁ።>

1
02/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 \v 9 8 «በሰምርኔስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤<እነዚህ መጀመሪያም መጨረሻም የሆነው የእርሱ ቃሎች ናቸው፤ሞቶ የነበረው፥እንደ ገና ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፤9''' መከራህንና ድኽነትህንም አውቃለሁ፤ነገር ግን ባለጠጋ ነህ፤የሰይጣን ማኅበር ሆነው እያለ፥አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።

1
02/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 \v 11 10 ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ፤እነሆ፤ ትፈተኑ ዘንድ ዲያብሎስ ከእናንተ እንዳንዶቻችሁን ወደ ወኅኒ ይጥላችኋል፤ለአስር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስም ታማኝ ሁን፤እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሀለሁ። 11 ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል የሚነሳም በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።>

1
02/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 \v 13 12 «በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤<እነዚህ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ካለው የተነገሩ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤13''' የሰይጣን ዙፋን ባለበት በዚያ እንደምትኖር አውቃለሁ፤ነገር ግን ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ መካከል በተገደለው በታማኙ ምስክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።

1
02/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 \v 15 14 ነገር ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው ማሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን የመከረው የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ። 15 እንደዚሁም የኒቆላውያንን ትምህርት አጥብቀው የያዙ ሰዎች እንኳ በአንተ ዘንድ አሉ።

1
02/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
16 ስለዚህ ንስሓ ግባ፤አለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ከአፌም በሚወጣው ሰይፍ አዋጋቸዋለሁ። 17 ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤እንደዚሁም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈብትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።>

1
02/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 \v 19 18 «በትያጥሮን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤<እነዚህ የእሳት ነበልባል የመሰሉ ዓይኖችና በእሳት እንደ ናስ ያሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤19''' ሥራህን አውቃለሁ፤ ፍቅርህንና እምነትህን፥ አገልግሎትህንና በትዕግሥት መጽናትህን፥በቅርብ የሠራኽ ሥራ በመጀመሪያ ካደረግኽው እንደሚበልጥም አውቃለሁ።

1
02/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 \v 21 20 ነገር ግን የምነቅፍብህ አንድ ነገር አለኝ፤ራሷን ነቢይት ብላ የምትጠራውን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል። ይህች ሴት በትምህርትዋ አገልጋዮቼ ሴሰኛ እንዲሆኑና ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉ ታስታቸዋለች። 21 ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር ፤ይሁን እንጂ ከርኩሰትዋ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም።

1
02/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 \v 23 22 እነሆ በሥቃይ አልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩት እርስዋ ከፈጸመችው ነገር ንስሓ ካልገቡ በስተቀር በከባድ ሥቃይ እንዲወድቁ አደርጋለሁ። 23 ልጆችዋን በሞት እቀጣለሁ፤በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሰውን ሐሳብና ፍላጎትን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ። ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላለሁ።

1
02/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 24 \v 25 24 ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉ እንዲሁም አንዳንዶች የሰይጣን ጥልቅ ምስጢር ነው የሚሉትን ነገር ለማታውቁ በትያጥሮን ለምትኖሩ ለቀራችሁት ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም።> 25 ሆኖም እስክመጣ ድርስ ያላችሁን ነገር አጸንታችሁ ጠብቁ።

1
02/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 26 \v 27 \v 28 \v 29 26 ድል ለነሳው፥ሥራዬንም እስከ መጨረሻ ለሚሠራ ለእርሱ በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ። 27 በብረት በትር ይገዛቸዋል፤እንደ ሸክላ ዕቃም ቀጥቅጦ ያደቃቸዋል። 28 ከአባቴ እንደተቀበልሁት እኔ ደግሞ ለእርሱ የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ። 29 ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ።>

1
03/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
1«በሰርዴስ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤<ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ በማለት ይናገራል፤«ሥራህን ዐውቃለሁ፤ሕያው እንደሆንህ የሚገልጽ ዝነኛ ስም አለህ፤ነገር ግን ሞተሃል። 2 ሥራህን በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆኖ ስላላገኘሁት ንቃ፤ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮች አጽና።

1
03/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
3 እንግዲህ ምን እንደተቀበልህና ምን እንደሰማህ አስታውስ፤ጠብቀው፤ንስሓም ግባ። ነገር ግን ባትነቃ ፥እንደ ሌባ እመጣለሁ፤በምን ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም። 4 ነገር ግን በሰርዴስ ልብሳቸውን ያላቆሸሹ ጥቂት ሰዎች አሉ። የተገባቸውም ስለ ሆነ፥ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።

1
03/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 \v 6 5 ድል የሚነሳ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ ፈጽሞ አልደመስሰውም፤ይልቁን በአባቴና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሰክራለሁ። 6 ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ይሚናገረውን ስማ።»

1
03/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 \v 8 7 «በፊላደልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥የሚከፍት እርሱ የከፈተውን ማንም የማይዘጋ፥የሚዘጋ እርሱ የዘጋውን ማንም ሊከፍት የማይችል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፤8 ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።

1
03/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 \v 11 9 እነሆ፤አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉት እነዚያ ከሰይጣን ማኅበር የሆኑት ውሸተኞች ናቸው። እነርሱንም እኔ እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ መጥተው በእግርህ እንዲወድቁ አደርጋለሁ። 10 በትዕግሥ እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ ፥በምድር የሚኖሩትን ይፈትን ዘንድ በዓለም ላይ ሁሉ ሊመጣ ካለው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ። 11 በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።

1
03/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
12 ድል ለሚነሳው በአምላኬ ቤተ መቅደስ ውስጥ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ከዚያም ከቶ አይወጣም። በእርሱም ላይ የአምላኬን ስም፥የአምላኬን ከተማ ስም ይኽውም ከአምላኬ ዘንድ ከሰማይ የምትርድዋ የአዲሲቷን አየሩሳሌም ስም እና የእኔን አዲስ ስም እጽፋለሁ። 13 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።>

1
03/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
14 «በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤< ይህም በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ገዥ እንዲሁም እውነተኛና ታማኝ ምስክር ከሆነው ቃሉም አሜን ከሆነው የተነገረ ነው፤ 15 ሥራህን አውቃለሁ፤በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም ይሆን ነበር። 16 እንግዲህ ትኩስ ወይም በራድ ሳትሆን በመካከል ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

1
03/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 \v 18 17«እኔ ሀብታም ነኝ፤ብዙ ገንዘብ አለኝ፤የጎደለኝ ምንም ነገር የለም» ትላለህ፤ነገር ግን እጅግ ጎስቋላ፥ምስኪን፥ድኻ፥ዕውርና የተራቆትህ እንደሆንህ አታውቅም። 18 ሀብታም ትሆን ዘንድ በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥የራቁትነትህን ሐፍረት ለመሽፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥አጥርተህ ለማየትም ዐይንህን እንድትኳል እመክርሃለሁ።

1
03/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 \v 20 19 እኔ የምወዳቸውን እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ እቀጣቸዋለሁ፤ አስተምራቸዋለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ንስሓም ግባ። 20 እነሆ፤በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምጼን ሰምቶ ቢከፍትልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

1
03/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
21 እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ። 22 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።»

1
04/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 4 \v 1 \v 2 \v 3 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ። 2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር። 3 በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር።

1
04/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 \v 5 4 በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር። 5 ከዙፋኑም የመብረቅ ብልጭታና የነጎድጓድ ድምፅ ወጣ። በዙፋኑም ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።

1
04/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 6 እንደዚሁም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት እጅግ የጠራ ባሕር ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ ሁሉ ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።

1
04/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 \v 8 7 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር። 8 አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር።

1
04/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 \v 11 9 ሕያዋን ፍጡራኑም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ክብር፥ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፥ 10 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ሰገዱ፤አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው፥ 11«ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።

1
05/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 5 \v 1 \v 2 1በዙፋኑም ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ከፊትና ከጀርባ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሓፍ አየሁ። 2 አንድ ብርቱ መልአክ፥«መጽሓፉን ሊከፍት፥ ማኅተሙን ሊፈታ የተገባው ማን ነው?» ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።

1
05/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 \v 4 \v 5 3 በሰማይ ቢሆን በምድር ወይም ከምድር በታች መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ ማንም አልቻለም። 4 መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ የተገባው ማንም ስላልተገኘ፥አምርሬ አለቀስሁ። 5 ነገር ግን ከሽማግሌዎች አንዱ፥«አታልቅስ፤እነሆ! ከዳዊት ሥር፥ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ መጽሓፉን ይከፍትና ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል» አለኝ።

1
05/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 \v 7 6 በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንዲሁም በሽማግሌዎች መካከል አንድ ታርዶ የነበረ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ። እርሱም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤እነዚህም በምድር ሁሉ ላይ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።7 ሄዶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልል መጽሓፉን ወሰደ።

1
05/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 ጥቅልል መጽሓፉንም በሚወስድበት ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገና እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበት የወርቅ ዕቃ ይዘው ነበር።

1
05/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 9 እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል። 10 አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»

1
05/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 \v 11 ከዚያም በኋላ ስመለከት፥በዙፋኑ፥በሕያዋኑ ፍጡራን እና በሽማግሌዎች ዙሪያ የብዙ መላእክት ድምፅ ሰማሁ፤ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር። 12 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።

1
05/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 \v 14 13 በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤ 14 አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፥«አሜን» አሉ፤ሽምግሌዎችም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።

1
06/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 6 \v 1 \v 2 1 ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ « ና!» ሲል ሰማሁ። 2 አየሁም ፤እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ባላዩ ላይ የተቀመጠውም ቀስት ይዞ ነበር፤አክሊልም ተሰጠው። እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ድል ይነሳ ዘንድ ወጣ።

1
06/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 \v 3 በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር« ና!» ሲል ሰማሁ። 4 ከዚያም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤በፈረሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርስ ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲያስወግድ ሥልጣን ተሰጠው፤ትልቅ ሰይፍም ተሰጠው።

1
06/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 \v 6 5 በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር «ና!» ሲል ሰማሁ፤ ጥቁር ፈረስ አየሁ፤በፈረሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር። 6 ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን የመጣ የሚመስል ድምፅ፥«አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፥ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ነገር ግን ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ» ሲል ሰማሁ።

1
06/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 \v 8 7 በጉ አራተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ የአራተኛው ሕያው ፍጡር ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ። 8 ከዚያም በኋላ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤በላዩም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ተብሎ ይጠራ ነበር፤ሲኦልም ይከተለው ነበር። ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ በሰይፍ፥በረሃብ፥ በበሽታ፥በዱር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።

1
06/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 \v 11 9 በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ። 10 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር። 11 ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።

1
06/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 \v 13 \v 14 12 በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ አየሁ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ፀሐይም እንደ ጥቁር ጨርቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ እንደ ደም ቀላች። 13 የበለስ ዛፍ ኀይለኛ ነፋስ በሚወዘውዛት ጊዜ በላይዋ ያለ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ ሁሉ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ። 14 ሰማይም እንደ ብራና እየተጠቀለለ ተወገደ፤ እያንዳንዱ ተራራና ደሴት ከስፍራው ተነቀለ።

1
06/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 \v 16 \v 17 15 ከዚያም በኋላ የምድር ነገሥታት፥ታላላቅ ሰዎች፥ የጦር መኮንኖች፥ ሀብታሞች፥ብርቱዎች፥ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ። 16 ለተራሮችና ለዐለቶችም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤« በላያችን ላይ ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት፥ከበጉም ቁጣ ሰውሩን 17 ታላቁ የቁጣቸው ቀን ስለ መጣ ማን መቆም ይችላል?»

1
07/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 7 \v 1 \v 2 \v 3 1 ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱም የምድር ማዕዘን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም በምድር ቢሆን በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ፈጽሞ ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር። 2 የሕያው አምላክ ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክ ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ። እርሱም ምድርንና ባሕርን ይጎዱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኽ፥3 « በአምላካችን አገልጋዮች ግምባር ላይ ማኅተም እስክናደርግ ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን እንዳትጎዱ » አለ።

1
07/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 \v 5 \v 6 4 ከእስራኤል ሕዝብ ነገድ ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ እንደ ሆነ ሰማሁ። 5 ከይሁዳ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሮቤል ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከጋድ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥6 ከአሴር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ

1
07/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 \v 8 7 ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥8 ከዛብሎን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከዮሴፍ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከብንያም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።

1
07/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 9 ከዚህ በኋላ ከሕዝብ፥ከነገድ፥ከወገንና ከቋንቋ ሁሉ የመጡ ቁጥራቸው ማንም ሊቆጥረው የማይችል አጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ በእጃቸውም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው አየሁ። 10 በታላቅ ድምፅም « ማዳን፥ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!» እያሉ ይጮኹ ነበር።

1
07/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 \v 12 11 መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑ እና በሽማግሌዎች ዙሪያ እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤እነርሱም በመሬት ላይ ወድቀው በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፥12 « አሜን! ውዳሴ፥ ክብር፥ጥበብ፥ምስጋና፥ኀይልና ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ይሁን፤አሜን» ይሉ ነበር።

1
07/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 \v 14 13 ከዚያም በኋላ ከሽማግሌዎች አንዱ፥«እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱ እነማናቸው ከየትስ የመጡ ናቸው?» በማለት ጠየቀኝ፤14 እኔም «ጌታ ሆይ፥አንተ ታውቃለህ» አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤«እነዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ አልፈው የመጡ ናቸው፤ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው በማንጻት ነጭ አድርገዋል።

1
07/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 \v 16 \v 17 15 ክዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መሆን ችለዋል፤ እርሱንም በመቅደሱ ውስጥ ቀንና ሌሊት ያመልኩታል። በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል። 16 እነርሱም ከእንግዲህ አይራቡም፤አይጠሙምም። ፀሐይ አያቃጥላቸውም፤ሙቀትም አያሰቃያቸውም። 17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል።»

View File

@ -1,4 +1,7 @@
<<<<<<< HEAD
<<<<<<< HEAD
=======
>>>>>>> 4ed441c5a0f92f36644647f6de50dd988cef6e6b
## License
This work is made available under a Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 International License (http://creativecommons.org/licenses/by-sa/4.0/).
@ -14,6 +17,7 @@ This work is made available under a Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0
**Attribution** - You must attribute the work as follows: "Original work available at https://door43.org/." Attribution statements in derivative works should not in any way suggest that we endorse you or your use of this work.
**ShareAlike** - If you remix, transform, or build upon the material, you must distribute your contributions under the same license as the original.
<<<<<<< HEAD
=======
# License
@ -43,3 +47,5 @@ You do not have to comply with the license for elements of the material in the p
No warranties are given. The license may not give you all of the permissions necessary for your intended use. For example, other rights such as publicity, privacy, or moral rights may limit how you use the material.
>>>>>>> 300c92f80157830ee55516ae4fac119ccc92a1a5
=======
>>>>>>> 4ed441c5a0f92f36644647f6de50dd988cef6e6b

View File

@ -35,7 +35,8 @@
"translators": [
"Girum",
"Pr. Ashebir",
"Tizita Zenebe"
"Tizita Zenebe",
"Getachew W"
],
"finished_chunks": [
"08-01",