am_rev_text_ulb/07/15.txt

1 line
693 B
Plaintext

\v 15 \v 16 \v 17 15 ክዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መሆን ችለዋል፤ እርሱንም በመቅደሱ ውስጥ ቀንና ሌሊት ያመልኩታል። በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል። 16 እነርሱም ከእንግዲህ አይራቡም፤አይጠሙምም። ፀሐይ አያቃጥላቸውም፤ሙቀትም አያሰቃያቸውም። 17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል።»