am_rev_text_ulb/06/09.txt

1 line
922 B
Plaintext

\v 9 \v 10 \v 11 9 በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ። 10 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር። 11 ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።