am_rev_text_ulb/04/07.txt

1 line
750 B
Plaintext

\v 7 \v 8 7 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር። 8 አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር።