10 lines
1.1 KiB
Markdown
10 lines
1.1 KiB
Markdown
# ተመስጦ
|
||
|
||
ተመስጦ የሚባለው ሰውየው እንቅልፍ ላይ ባይሆንም፣ አንድ ሌላ ነገር እየተመለከተ ወይም እየተለማመደ ከመሆኑ የተነሣ በዙሪያው ስላለው ነገር ግንዛቤ የሚያጣባት የአእምሮ ዝንባሌ ነው።
|
||
|
||
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል እግዚአብሔር በራእይ በተናገራቸው ጊዜ ጴጥሮስና ጳውሎስ የነበራቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአእምሮ ሁኔታ ያመለክታል።
|
||
* ጴጥሮስና ጳውሎስ ተመስጦ ውስጥ የሆኑት እየጸለዩ እያለ ነበር።
|
||
* ተመስጦ ውስጥ እንዲሆኑ ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።
|
||
* “ተመስጦ” – “ራእይ” ከሚለው ቃል የተለየ በመሆኑ፣ ትርጕሙም የተለየ መሆን አለበት።
|
||
* “ተመስጦ ወደቀበት” ማለት ሳይተኛ ወይም ሳያንቀላፋ፣ “በድንገት እንደ እንቅልፍ ያለ ሰመመን ውስጥ ሆነ” ማለት ነው።
|