am_tw/bible/other/trance.md

1.1 KiB
Raw Permalink Blame History

ተመስጦ

ተመስጦ የሚባለው ሰውየው እንቅልፍ ላይ ባይሆንም፣ አንድ ሌላ ነገር እየተመለከተ ወይም እየተለማመደ ከመሆኑ የተነሣ በዙሪያው ስላለው ነገር ግንዛቤ የሚያጣባት የአእምሮ ዝንባሌ ነው።

  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል እግዚአብሔር በራእይ በተናገራቸው ጊዜ ጴጥሮስና ጳውሎስ የነበራቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአእምሮ ሁኔታ ያመለክታል።
  • ጴጥሮስና ጳውሎስ ተመስጦ ውስጥ የሆኑት እየጸለዩ እያለ ነበር።
  • ተመስጦ ውስጥ እንዲሆኑ ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።
  • “ተመስጦ” “ራእይ” ከሚለው ቃል የተለየ በመሆኑ፣ ትርጕሙም የተለየ መሆን አለበት።
  • “ተመስጦ ወደቀበት” ማለት ሳይተኛ ወይም ሳያንቀላፋ፣ “በድንገት እንደ እንቅልፍ ያለ ሰመመን ውስጥ ሆነ” ማለት ነው።