1.1 KiB
1.1 KiB
ተመስጦ
ተመስጦ የሚባለው ሰውየው እንቅልፍ ላይ ባይሆንም፣ አንድ ሌላ ነገር እየተመለከተ ወይም እየተለማመደ ከመሆኑ የተነሣ በዙሪያው ስላለው ነገር ግንዛቤ የሚያጣባት የአእምሮ ዝንባሌ ነው።
- አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል እግዚአብሔር በራእይ በተናገራቸው ጊዜ ጴጥሮስና ጳውሎስ የነበራቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአእምሮ ሁኔታ ያመለክታል።
- ጴጥሮስና ጳውሎስ ተመስጦ ውስጥ የሆኑት እየጸለዩ እያለ ነበር።
- ተመስጦ ውስጥ እንዲሆኑ ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።
- “ተመስጦ” – “ራእይ” ከሚለው ቃል የተለየ በመሆኑ፣ ትርጕሙም የተለየ መሆን አለበት።
- “ተመስጦ ወደቀበት” ማለት ሳይተኛ ወይም ሳያንቀላፋ፣ “በድንገት እንደ እንቅልፍ ያለ ሰመመን ውስጥ ሆነ” ማለት ነው።