# ተመስጦ ተመስጦ የሚባለው ሰውየው እንቅልፍ ላይ ባይሆንም፣ አንድ ሌላ ነገር እየተመለከተ ወይም እየተለማመደ ከመሆኑ የተነሣ በዙሪያው ስላለው ነገር ግንዛቤ የሚያጣባት የአእምሮ ዝንባሌ ነው። * አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል እግዚአብሔር በራእይ በተናገራቸው ጊዜ ጴጥሮስና ጳውሎስ የነበራቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአእምሮ ሁኔታ ያመለክታል። * ጴጥሮስና ጳውሎስ ተመስጦ ውስጥ የሆኑት እየጸለዩ እያለ ነበር። * ተመስጦ ውስጥ እንዲሆኑ ያደረገው እግዚአብሔር ነበር። * “ተመስጦ” – “ራእይ” ከሚለው ቃል የተለየ በመሆኑ፣ ትርጕሙም የተለየ መሆን አለበት። * “ተመስጦ ወደቀበት” ማለት ሳይተኛ ወይም ሳያንቀላፋ፣ “በድንገት እንደ እንቅልፍ ያለ ሰመመን ውስጥ ሆነ” ማለት ነው።