am_tw/bible/other/ruin.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

መፍረስ፣ ፍርስራሽ

አንድ ነገር፣ “ማፍረስ” ያንን ነገር ማበላሸት፣ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ማለት ነው። “ፍርስራሽ” እንዲፈርስ ከተደረገው ነገር የቀረ ክምር ነው።

  • የእግዚአብሔር ቀን፣ ዓለም ላይ የሚፈረድበትና ዓለም የሚቀጣበት “የመፍረስ ቀን” እንደ ሆነ ነቢዩ ሰፎንያስ ተናግሯል።
  • እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች ጥፋትና መፍረስ እንደሚጠብቃቸው መጽሐፈ ምሳሌ ያመለክታል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መፍረስ” የሚለውን፣ “ማጥፋት” ወይም፣ “ማበላሸት” ወይም “ከጥቅም ውጪ ማድረግ” ወይም፣ “መስበር” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ፍራሽ” ወይም “ፍርስራሽ” “ክምር” ወይም፣ “የፈራረሱ ሕንፃዎች” ወይም፣ “የተደመሰሰ ከተማ” ወይም፣ “ውድመት” ወይም፣ “ስብርባሪ” ወይም “ጥፋት” በማለት መተርጎም ይቻላል።