# መፍረስ፣ ፍርስራሽ አንድ ነገር፣ “ማፍረስ” ያንን ነገር ማበላሸት፣ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ማለት ነው። “ፍርስራሽ” እንዲፈርስ ከተደረገው ነገር የቀረ ክምር ነው። * የእግዚአብሔር ቀን፣ ዓለም ላይ የሚፈረድበትና ዓለም የሚቀጣበት “የመፍረስ ቀን” እንደ ሆነ ነቢዩ ሰፎንያስ ተናግሯል። * እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች ጥፋትና መፍረስ እንደሚጠብቃቸው መጽሐፈ ምሳሌ ያመለክታል። * እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መፍረስ” የሚለውን፣ “ማጥፋት” ወይም፣ “ማበላሸት” ወይም “ከጥቅም ውጪ ማድረግ” ወይም፣ “መስበር” ብሎ መተርጎም ይቻላል። * እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ፍራሽ” ወይም “ፍርስራሽ” – “ክምር” ወይም፣ “የፈራረሱ ሕንፃዎች” ወይም፣ “የተደመሰሰ ከተማ” ወይም፣ “ውድመት” ወይም፣ “ስብርባሪ” ወይም “ጥፋት” በማለት መተርጎም ይቻላል።