am_tw/bible/other/ruin.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መፍረስ፣ ፍርስራሽ
አንድ ነገር፣ “ማፍረስ” ያንን ነገር ማበላሸት፣ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ማለት ነው። “ፍርስራሽ” እንዲፈርስ ከተደረገው ነገር የቀረ ክምር ነው።
* የእግዚአብሔር ቀን፣ ዓለም ላይ የሚፈረድበትና ዓለም የሚቀጣበት “የመፍረስ ቀን” እንደ ሆነ ነቢዩ ሰፎንያስ ተናግሯል።
* እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች ጥፋትና መፍረስ እንደሚጠብቃቸው መጽሐፈ ምሳሌ ያመለክታል።
* እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መፍረስ” የሚለውን፣ “ማጥፋት” ወይም፣ “ማበላሸት” ወይም “ከጥቅም ውጪ ማድረግ” ወይም፣ “መስበር” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
* እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ፍራሽ” ወይም “ፍርስራሽ” “ክምር” ወይም፣ “የፈራረሱ ሕንፃዎች” ወይም፣ “የተደመሰሰ ከተማ” ወይም፣ “ውድመት” ወይም፣ “ስብርባሪ” ወይም “ጥፋት” በማለት መተርጎም ይቻላል።