initial conversion

This commit is contained in:
Larry Versaw 2021-03-04 12:07:37 -07:00
parent 1ca8d6b1a2
commit ca0e95876f
1050 changed files with 7984 additions and 1 deletions

View File

@ -1,3 +1,3 @@
# am_tw
Amharic Translation Words
Amharic Translation Words

6
bible/kt/abomination.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ጸያፍ
* ርኩስ ወይም የተጠላ ነገርን ለመግላጽ “ጸያፍ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
* ግብፃውያን የዕብራውያን ሰዎችን እንደ “ጸያፍ” ይቆጥሩ ነበር። ይህም ማለት ግብጻውያን ዕብራውያንን ይጠሏቸው ነበር፤ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ወይም አጠገባቸው ለመሆን አይፈልጉም ነበር ማለት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ “ለያህዌ ጸያፍ” ከሚላቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ውሸት ትዕቢት፣ሰዎችን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ፣ጣዖት ማምለክ፣መግደል፣የዝሙት ኅጢአቶችና ከወንድ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የመሳሰሉት ናቸው።
* የመጨረሻ ቀኖችን አስመልክቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ኢየሱስ በእግዚአብሔር ላይ በዓመፅ የአምልኮ ቦታውን ለማርከስ ስለማቆመው ትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውን፣ የጥፋት ርኩሰት አመልክቷል።

6
bible/kt/adoption.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ልጅነት/ልጅ አድርጎ መቀበል
“ልጅነት” የተሰኘው ቃል አንድን ሰው በተፈጥሮ ወላጆቹ ያልሆኑ ሰዎች ሕጋዊ ልጅ የማድረግ ሂደት ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ “ልጅነት” ወይም “ልጅ አድርጎ መውሰድ” የተሰኙትን ቃሎች እግዚአብሔር ሰዎችን እንዴት የቤተሰብ አካል፣የእርሱ መንፈሳዊ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደሚያደርግ ለመግለጽ በምሳሌያዊ መልኩ ይጠቀምበታል።
* ልጆች እንደሆኑ ተቀባይነት በመግኘታቸው አማኞች የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች መብት ሁሉ ያላቸው ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሾች ሆነዋል።

8
bible/kt/adultery.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ዝሙት፣ዘማዊነት፣ዘማዊ፣ዘማዊት
“ዝሙት” አንድ ያገባ ሰው የትዳር ጓደኛው ካልሆነች ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን ኃጢአት ያመለክታል። “ዘማዊነት”የዚህ ዐይነት ተግባርን ወይም ይህን ኃጢያት የሚያደርግ ሰው ድትጊት ያመለክታል።
* አንዳንዴ “ዘማዊት” የሚለው ቃል ዝሙት የፈጸመችው ሴት መሆንዋን ለይቶ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
* ዝሙት ባልና ሚስት በጋብቻ ኪዳን አንዳቸው ለሌላው ያገቡትን ቃል ያፈርሳል።
* ዝሙት እንዳያደርጉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዟል።
* ብዙውን ግዜ ዘማዊነት የሚለው ቃል የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆኑበትን በተለይ ደግሞ ሐሰተኛ አማልክትን ያመለከበትን ሁኔታ ለመግለጽ ምሳሌያዊ በሆነ ቋንቋ ጥቅም ላይ ውሏል።

6
bible/kt/almighty.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ሁሉን ቻይ
“ሁሉን ቻይ” የሚለው ቃል በቃል “ኃይል ሁሉ የእርሱ የሆነ” ማለት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም የሚያመልክተው እግዚኣብሔርን ነው።
* “ሁሉን ቻይ” ወይም “ሁሉን ቻይ” የሚለው መጠለያ የሚመለከተው እግዚአብሔርን ነው፤ እርሱ በሁሉም ላይ ፍጹም ኅይልና ሥልጣን ያለው መሆኑን ይገለጻል።
* ይህ ቃል “ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር” ወይም “እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ” ወይም “ሁሉን ቻይ ጌታ” ወይም፣ “ሁሉን ቻይ ጌታ እግዚአብሔር” በተሰኙት መጠሪያዎች እግዚአብሔር ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል።

7
bible/kt/altar.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# መሠዊያ
መሠዊያ ለእግዚአብሔር መባ(ስጦታ)እንዲሆን እስራኤላውያን እንስሳትና የእህል ዓይነቶችን የሚያቃጥልበት ከፍ ብሎ የሚሠራ ነገር ነው።
* በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የቦካ በመካብ ወይም ክምር እስኪሆን ድረስ ድንጋዮችን በመደርደር ቀለል ያሉ መሠዊያዎች ይሠሩ ነበር።
* ከእንጨት ሳጥን መሰል መሠዊያዎች ይሠሩና በኋላ እንጨቱ ወርቅን፣ናስን ውይም መዳብን በመሳሰሉ ነገሮች ይለበጡ ነበር።
* እስራኤላውያን በነበሩበት አካባቢ የነበሩት ሕዝቦችም ለአማልክቶቻቸው መዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያዎች ይሠሩ ነበር።

7
bible/kt/amen.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# አሜን፣በእውነት ይሁን
“አሜን” የሚለውለንድ ሰው የተናገረውን አጽንዖት ለመስጠት ወይም ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። ኢያሱስ ይህን ቃል ሲናገር ብዙውን ጊዜ አሜን ይሁን እንደ ማለት ነው።
* ጸሎት መጨረሻ ላይ “አሜን” ከተባለ ከጸሎት ጋር መስማማትን ወይም ጸሎት እንዲፈጽም መፈለግን ያሳያል።
* በትምህርቱ የተናገረውን ለማስረገጥ ኢየሱስ “አሜን” በሚለው ተጠቅሟል ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያደርግ የነበረው ከተናገረው ጋር የሚያያዝ ሌላ ትምህርት ለማቅረብ፣ “እኔ እንዲህ እላችኋለው” በሚልበት ጊዜ ነው።
* አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ይህን፣ በእውነት ይሁን በማለት ተርጉመውታል ለተወሰነ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ይተነገረው ቅን ወይም እውነት መሆኑን ለመግለጥ ጥቅም ላይ ይውላል።

13
bible/kt/angel.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,13 @@
# መልአክ፤የመላእክት አለቃ
መልአክ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ሃያል መንፈዊ ፍጡር ነው፤መላአኮች የተፈጥጠሩት እርሱ የሚነግራቸውን በማድረግ እግዚአብሔርን እንድያገለግሉ ነው፤የመላክት አለቃ ሌሎች መላአኮችን ሁሉ የሚያዝዝ ወይም የ መልአክን ያመለክታል።
* ቃል በቃል መልአክ መልክትኛ ማለት ነው፤
* የመላእክት አለቃ ማለት ዋና መልእክትኛ ማልት ነው፤መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመላዕክቱ አለቃ ተበሎ ሚካኤል ብቻ ነው፤
* ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው መላእኮች መልክቶችን ከእግዚአብሔር ለሰዎች አድርሰዋል፤እነዚህ መልክቶች እግዚአብሔር ሰዎች ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ ለሰዎች መመሪያ መስጠትን ይጨምራል።
* መላአክቱ ወደ ራት የሚሆኑ ነገሮችን ወይም ቀደም ሲል የሆኑ ነገሮችን በተመለከተም ለሰዎች ተናግረዋል።
* መላእክቱ የእግዚአብሔር ሥልጣን አላቸው፤የእርሱ ተወካዩች እንደ መሆናቸው መጠን መጽሐፍ ቅድስ ውስጥ አንዳንዴ ልክ እንደ ራሱ እንደ እግዚአብር ተናግርዋል።
* መላእክት የእግዚአበሔርን የሚያገለግሉት ሌላው መንግድ ሰዎችን በመጠንቅና ሰዎችን በማበረታት ነው፤
* የያህዌ(የእግዚአብሔር) መልአክ ይ ለየት ያለ ሐርግ ከአንድ በላይ ትርጉም አልው፤1)’’ያህዌን የሚወክል መልአክ ወይም ያህዌን የሚያገለግል መልክተኛ ማለት ሊሆን ይችላል።
ለሰወች ሲናገር በመልአክ ተመስሎ የመጣ ራሱ እግዚአብሔር ሊያመለክት ይችላል፤አንድ መልአክ ያህዌ ራሱ የተናገረ ያህል’’እኔ’’እያለ የተናገረው ለምን እንደ ነበር ከእነዚህ ትርጉሞች አንዱ በቂ ገለጻ ይሰጠን ይሆናል።

10
bible/kt/anoint.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# መቃባት፤የተቀባ
“መቀባት” የሚለው ቃል ሰውን ወይም አንድን ነገር በ ማሰብ ወይም ላይ ላይ ዘይት ማፍሰስ ማለት ነው፤አንዳንዴ ዘይቱ ከተለዩ ቅመሞች ጋር ስለሚቀላቀል በጣም ጣፋጭ መዕዛ ያለው ሽቶ ይሆናል፤ቃሉ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ መንፈስ ቅዱስ ሰው መምረጡንና ሃይል ማስታጠቁን ያመለክታል።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን ለ የእግዚአብሔር እገልግሎት ሰዎችን ለመለየት ካህናት ነገስታትናነቢያት ዘይት ይቀቡ ነበር።
* እግዚአብሔርን ለማምለክና እርሱን ለማክበር የተለዩ መሆናቻውን ለማሳየት መሠዊያና መገናኛ ድን ዅኑን የመሳሰሉ ነገሮች ዘይት ይቀቡ ነበር፤
* በአዲስ ኪዳን የተመሙ ሰዎች እንዲፈወሱ ዘይት ይቀቡ ነበር፤እርሱም ማምልከዎን ለማሳየት አንዲት እየሱስን ጥሩ ሽታ ባለው ዘይት እንድ ቅባት አዲስ ኪዳን ሁለት ጊዜ
* እየሱስ ከሞተ በሃላ ዘይትና ቅመማ ቅመም በመቀባት ወዳጆችቹ ሥ ለቀብር አዘጋጁ፤
* የዕብራይስጡ መሲሕ እና የግሪኩ ክርስቶስ፥የተቀባ የሚል ትርጉም አላችው፤
* ነቢይ ሊቀ ካህንና ንጉሥ እንደሆነ፤የተመረጠውና የተቀባው መሲሑ እየሱስ ነው፤

7
bible/kt/antichrist.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# የክርስቶስ ተቃዋሚ
የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚለው አገላለጽ እየሱስ ክርስቶስንና ሥራውን የሚቃወም ሰውን ወይም ትምህርትን ነው የሚያመለክተው በዓለም ውስጥ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አሉ።
* አንድ ሰው እየሱስ መሲሕ አይደለም በማለት ሰዎችን የሚያሳሳትና እርሱ እ ሰውም መሆኑን የሚክድ ሰው ከሆነ ያ ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን ሐዋርያው ዩሐንስ ጵፎአል።
* የእየሱስ ሥራ የሚቃወም ግልጽ ያልሆነ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በዓለም እንዳለ አዲስ ኪዳን ያስተምራል።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የዩሐንስ ራእይ በመጨረሻው ዘመን የሚገለጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚባል ሰው እንደሚኖር ይናገራል፤ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማጥፋት ይሞክራል ግን በእየሱስ ይሸነፋል።

7
bible/kt/apostle.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ሐዋርያ ፣ ሐዋርያነት
ሐዋርያት ስለ እግዚአበሔር ስለ መንግሥቱ ለሰዎች እንዲሰበኩ እየሱስ የላካቸው ሰዎች ነበሩ፤ሐዋርያነት የሚለው ቃል ሐዋርያነት ለመሆን የተመረጡ ሰወች የነበራቸውን ቦታና ስልጣን ያመለክታል።
* ሐዋርያ የሚለው ቃል ለአንድ ለተለየ ዓላማ የተላከ ማለት ነው፤ሐዋርያ እርሱን የላከው ሥልጣን አለው።
* ለእየሱስ በጣም ቅርበ የነበሩ አሥራ ሁለት ደቀመዛሙርት የመጀመሪዎቹ ሐዋርያት ሆኑ፤ጻውሎስንና ያዕቆበን የመሳሰሉ ሰዎችም ሐዋርያት ሆነዋል።
* በእግዚአብሔር ሓይል ሐዋርያት አጋንንት ከሰዎች እንዲወጡ ማዘዝን ጨምሮ በድፍረት ወንጌልን ሰብከዋል፤የታመሙትን ፈውሰዋል።

9
bible/kt/appoint.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# መሾም፤ይሾም
መሾም እና የተሾመ የተሰኙት ቃላት አንድ የተለየ ተግባርን ወይም ተልኮን እንዲሁም አንድን ሰው መምረጥን ያመለክታል።
* መሾም እንደ የዘላለም ትይውን የመሳሰሉ ነገሮችን ለመቀብል መመረጥን ያመለክታል፤እንዲህ ማለት የዘላለምን ት
እንዲቀበሉ ተመርጠዋል ማለት ነው።
* የተወሰነው ጊዜ የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የመረጠውን ጊዜ ወይም አንዳች ነገር እንዲደረግ የታቀደ ጊዜን ያመለክታል።
* መሾም የሚለው ቃል አንድ ሰው አንዳች ነገርን እንዲያደርግ ማዘዝ ወይም ተልዕኮ መስጠት ማለት ሊሆንም ይችላል።

9
bible/kt/ark.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# ታቦት
* የቃል ኪዳኑ ታቦት፥ የኪዳኑ ሕግ ታቦት፥ የያህዌ (እግዚአብሔር) ታቦት፥ እነዚህ ቃሎች ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የያዘ በወርቅ የተለበጠ ይተለየ የእንጨት ሳጥን ያመለክታሉ። የአሮን በትርና መና የነበረበትንም ዕቃ ይይዛል።
* እዚህ ላይ፥ “ታቦት” የሚለው፥ “ሳጥን” ወይም፥ “ሰንዱቅ” ወይም፥ “መያዣ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
* በዚህ ሳጥን ወይም ሰንዱቅ ውስጥ ያሉ ነገሮች ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ያስታውሷቸዋል።
* የኪዳኑ ታቦት የሚቀመጠው፥ “ቅድስተ ቅዱሳን” ውስጥ ነበር
* የእግዚአብሔር ሐልዎት ወይም መገኘት ቅድስት ቅዱስን ውስጥ ካለው ከታቦቱ በላይ ነበር፤ እስራኤላውያንን በተመለከተ ለሙሴ የሚናገረው ከዚያ ነበር
* የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤተ መቅደሱ ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን በነበረበት ዘመን በዓመት አንዴ በስርዓት ቀን ወደታቦቱ መቅረብ የሚችል ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር።
* አንዳንድ ትርጉሞች፥ የኪዳኑ ታቦት የሚለውን ቃል በቃል፥ “የምስክሩ ታቦት” በማለት ተርጉመውታል። ይህ የሚያመለክተው አሥሩ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን ምስክር ከመሆናቸው አንጻር ነው “ የሕጉ ኪዳን” ተብሎም ተተርጉሟል።

7
bible/kt/atonement.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ቤዛነት፥ቤዛ
“ቤዛ” እና “ቤዛነት” ለሰው ልጆች ኃጢአት የሚከፈልና የእርሱን በኃጢአት መቆጣት የሚያበርድ መሥዋዕት እግዚአብሔር ያዘጋጀበትን ሁኔታ ያመለክታል
* በብሉይ ኪዳን ዘመን እንስሳን በመግደል ለእስራኤላውያን ኃጢአት የደም መሥውዕትን በማቅረብ ጊዜያዊ ቤዛ እንዲደረግ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር
* በአዲስ ኪዳን እንደተጻፈው እውነተኛና ዛላቂ የኃጢአት ቤዛ የክርስቶስ መስቀል ላይ ሞት ብቻ ነው
* ክርስቶስ የሞት ጊዜ ከኃጢአታቸው የተነሣ ሰዎች ሊቀበሉት ይገባ የነበረውን ቅጣት ወሰደ። በመሥዋዕታዊ ሞቱ የቤዛነት ዋጋ ከፈለ።

8
bible/kt/atonementlid.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# የስርየት መክደኛ
“የስርየት መክደኛ” ከወርቅ የተሠራ ጠፍጣፋ ነገር ሲሆን የታቦቱን የላይኛ ክፍል ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች “የስርየት መሸፈኛ” ይሉታል
* የስርየት መክደኛ 115 ሳንቲሜትር ርዝመትና 70 ሳንቲሜትር ስፋት ነበረው
* ከስርየት መክደኛው በላይ ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተነካኩ ሁለት የወርቅ ኪሩቤል ነበሩ
* ከስርየት መክደኛው በላይ፥ ከተዘረጉት የኪሩቤል ክንፎች በታች ከእስራኤላውያን ጋር እንደሚገናኝ ያህዌ ተናግሮአል። እንደሕዝቡ ተወካይ ይህን ማድረግ የተፈቀደለት ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር
* ይህ የስርየት መክደኛ አንዳንዴ፥ “የምሕረት መቀመጫ” ተብሎአል፤ እንዲህ የተባለበት ምክንያት ኃጢአተኛ የሰው ልጆችን ለመዋጀት የሚመጣው የእግዚአብሔር ምሕረት መተለለፊያ ስለሆነ ነው

6
bible/kt/authority.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ሥልጣን
“ሥልጣን” የተሰኘው ቃል አንድ ሰው ሌላው ሰው ላይ ያለውን ተፅዕኖ የማሳደር ወይም የመቆጣጠር ኅይልን ያመለክታል
* ነገሥታትና ሌሎች ገዦች በሚገዟቸው ሰዎች ላይ ሥልጣን አላቸው
* “ሥልጣን” የሚለው ቃል ሌሎች ላይ ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች፥ መንግስታትና ድርጅቶች ያመለክታል

6
bible/kt/baptize.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ማጥመቅ፥ ጥምቀት
አዲስ ኪዳን ውስጥ “ማጥመቅ” እና፥ “ጥምቀት” የተሰኙ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ከኃጢአት መንጻቱንና ከክርስቶስ ጋር መተባበሩን ለማሳየት ክርስቲያኑን ውሃ ውስጥ የመንከር ስርዓትን ያመለክታል
* ከውሃ ጥምቀት በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ፥ “በመንፈስ መጠመቅ” እና “በእሳት መጠመቅ” ስለመሳሰሉ ነገሮች ይናገራል
* በታላቅ መከራ ውስጥ ማለፍን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ “ጥምቀት” የተሰኘውም ቃል ጥቅም ላይ ውሏል

6
bible/kt/believe.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ማመን፥ አመነ፥ እምነት
“ማመን” እና “አመነ” በጣም የተያያዙ ቢሆንም በመጠኑ የሚለያይ ትርጉም አላቸው
* “ማመን” የሚለው ቃል፥ “እውነት መሆኑን ማወቅ” ወይም፥ “ትክክል መሆኑን ማወቅ” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል
* “አመነ” የሚለው ቃል፥ “ሙሉ በሙሉ መተማመን” ወይም፥ “መተማመንና መታዘዝ” ወይም፥ “በፍጹም ልብ መደገፍና መከተል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

7
bible/kt/beloved.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# የተወደደ
“የተወደደ” በሌላው ሰው የተወደደና ውድ የሆነ ሰውን የሚያሳይ የፍቅር መገለጫ ቃል ነው
* “የተወደደ” ቃል በቃል፥ “ የሚወደድ ሰው” ወይም፥ “ውድ የሆነ ሰው” ማለት ነው
* እግዚአብሔር ኢየሱስን፥ “የተወደደ” ወይም፥ “የምወደው ልጄ” ብሎታል
* ለአብያት ክርስቲያናት በጻፉት መልእክት ሐዋርያት አማኞችን “የተወደዳችሁ” በማለት ይጠሯቸው ነበር

8
bible/kt/birthright.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# የመወለድ መብት
“የመወለድ መብት” የተሰኘው ቃል ከቤተ ሰቡ የተወለዱ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ያለውን ክብር፣ ከቤተ ሰቡ መጠራትንና ሀብት መወሰድን መደበኛ መብት ያመለክታል።
* የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ያለው የመወለድ መብት ዕጥፍ የአባቱን ሀብት የመውሰድ መብትንም ይጨምራል።
* የአንድ ንጉሥ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ አባቱ ከሞተ በኋላ ሥልጣኑን ወስዶ የመግዛት የመወለድ መብት አለው።
* ኤሳው ብኵርናውን ወይም የመወለድ መብቱን ለታናሽ ወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠ። ከዚህም የትነሣ ከኤሳው ይልቅ ያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ የሚያገኘውን በረከት ወሰደ።
* የመወለድ መብት በቤተ ሰቡ የዘር ሐረግ ውስጥ የመጀምሪያ ሆኖ የመጠራት ክብርንም ይጨምራል።

7
bible/kt/blameless.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ነቀፋ የሌለበት
“ነቀፋ የሌለበት” የሚለው ቃል በቃል፣ “ነውር፣ እንከን” የሌለበት ማለት ነው። በፍጹም ልቡ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሰውን የሚያመለክት ቢሆንም፣ ያ ሰው ምንም ኃጢአት የለበትም ማለት አይደለም።
* አብርሃምና ኖኅ በእግዚአብሔር ፊት ነቀፋ የሌለባቸው ተብለዋል።
* “ ነቀፋ የሌለበት” ተብሎ የሚታወቅ ሰው እግዚአብሔርኝ በሚያስከብር መንገድ ይኖራል።
* አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደሚያመለክተው ነቀፋ የሌለበት ሰው፣ “እግዚአብሔርብ የሚፈራና ከክፋትም የራቀ” ነው።

7
bible/kt/blasphemy.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ስድብ፣ ተሰደበ
መጽሐፍ ቁስ ውስጥ፣ “ስድብ” እግዚአብሔርንና ሰውን በጣም በሚያንቋሽሽ መንገድ መናገርግን ያመለክታል። አንድን ሰው፣ “መስደብ” ሰዎች ሐሰት የሆነ መጥፎ ነገር እንዲያስቡ በዚያ ሰው ላይ ክፉ ነገር መናገር ማለት ነው።
* ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን መሳደብ ሲባል እርሱን ማማት ወይም እርሱን በተመለከተ እውነት ያልሆነ ነገርን በመናገር መሳደብን ወይም እርሱን በማያስከብር ሁኔታ ውስጥ መኖርን ያመለክታል።
* አንድ ሰው እግዚአብሔር ነኝ ቢል ወይም ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ሌላ እግዚአብሔር እንዳለ ቢናገር ያ ሰው ተሳድቦአል።
* አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች ሰዎችን ስለ መሰደብ የሚያመለክት ከሆነ ይህን “ሐሜት” በማለት ተርጕመውታል።

8
bible/kt/bless.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# መባረክ፣ ተባረክ፣ በረከት
አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፣ “መባረክ” በዚያ ሰው ወይም ነገር ላይ መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው።
* አንድን ሰው መባረክ በዚያ ሰው ላይ ጠቃሚ እና ቀና ነገር እንዲሆን ምኞትን መግለጽም ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጊዜ አባት ለልጆቹ የበረከት ቃል ይናገር ነበር።
* ሰዎች እግዚአብሔርን “ሲባርኩ” ወይም እግዚአብሔር እንዲባረክ ምኞታቸውን ሲገልጹ እርሱን እያመሰገኑ ነው ማለት ነው።
* “መባረክ” የሚለው ቃል ምግብ ከመበላቱ በፊት እንዲቀደስ ወይም ስለዚያ ምግብ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጥቅም ላይ ይውላል።

9
bible/kt/blood.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# ደም
“ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል።
* ደም የሕይወት ምሳሌ ነው፤ የደም መፍሰስ የሕይወት መጥፋት ወይም የሞት ምሳሌ ነው።
* ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሲያቀርቡ እንስሳ ያርዱና ደሙን መሠዊያው ላይ ያፈስሱ ነበር። ይህም ለሰዎች ኃጢአት ክፍያ እንዲሆን የእንስሳው ሕይወት መሥዋዕት የመሆኑ ምስላ ነበር።
* በመስቀል ላይ ሞቱ የኢየሱስ ደም ሰዎችን ከኃጢአታቸው የነጻቸዋል፤ ለኃጢአታቸው ይገባቸው የነበረው ቅጣት የመከፈሉ ምሳሌ ነው።
* “ሥጋና ደም” የሰው ልጆችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አንጋገር ነው።
* “ሥጋና ደም” በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።

9
bible/kt/boast.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# መመካት፣ ትምክህተኛ
“መመካት” በሰዎች ወይም በነገሮች በመመካት በትዕቢት መናገር ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ስለ አራስ በእብሪት መናገር ማለት ነው።
* “ትምክህተኛ” ሰው ስለ ራሱ በትዕቢት ይናገራል።
* በጣዖቶቻቸው በመመካታቸው እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገሥጾአል። በእውነተኛው አምላክ ይልቅ በግትርነት ጣዖቶቻቸውን እያመለኩ ነበር።
* መጽሐፍ ቅዱስ ሀብትን፣ ብርታትን፣ ፍሬያማ እርሻንና ሕጎቻቸውን በመሳሰሉ ነገሮች ስለሚመኩ ሰዎችም ይናገራል። ይህም ማለት እነዚህን ነገሮች የሚሰጥ እግዚአብሔር መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ፣ በእነዚህ ነገሮች ትዕቢት አድሮባቸዋል ማለት ነው።
* በእነዚህ ነገሮች ከመመካት ወይም ከመታመን ይልቅ እርሱን በማወቃቸው እንዲመኩ እግዚአብሔር አጥብቆ ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።
* ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ ስለ መመካት ይናገራል፤ ይህም ማለት እርሱ ስላደረገላቸው ሁሉ በእርሱ ደስ መሰኘትና እርሱን ማመስገን ማለት ነው።

10
bible/kt/body.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# አካል
“አካል” ቃል በቃል የሰው ወይም የእንስሳ ሥጋ ማለት ነው። ይህ ቃል አንድን ነገር ወይም በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለ ሰቦችን ለማመልከትም ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
* ቃል በቃል ሲወሰድ “አካል” የሞተ ሰው ወይም እንስሳን ይመለከታል። አንዳንዴ “የሞተ አካል” ወይም፣ “ሬሳ” ያመለክታል።
* የመጨረዓው የፋሲካ ራት ላይ ኢየሱስ፣ “ይህ ሥጋዬ ነው” በማለት ሲናገር፣ ለኃጢአታቸው ክፍያ ለመሆን. “የሚቆረሰውን” (የሚገደለውን) ሥጋዊ አካሉን ማመልከቱ ነበር።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች እንደ አንድ ቡድን፣ “የክርስቶስ አካል” ተብለው ተጠርተዋል።
* የሰው አካል ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ሁሉ፣ “የክርስቶስ አካል” ብዙ ግለ ሰብ አባሎች አሉት።
* በአንድነት እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር እንዲሆን ለማገዝ እያንዳንዱ አማኝ የክርስቶስ አካል ውስጥ የራሱ የሆነ ተግባር አለው።
* ኢየሱስ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች፣ “አካል ራስ (መሪ)” ተብሎአል። የአንድ ሰው ራስ አካሉ ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚናገር ሁሉ፣ እንደ “አካሉ” ብልቶች ክርስቲያኖችን የሚመራና አቅጣጫ የሚያስይዝ ኢየሱስ ነው።

13
bible/kt/bond.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,13 @@
# ማሰር፣ ማሰሪያ፣ አሰረ
“ማሰር” አንድን ነገር ጥብቅ አድርጎ ማሰር ወይም እንዳይበታተን አድርጎ መቋጠር ማለት ነው። አንድ ነገር የሚያስር ወይም እርስ በርስ የሚያያይዝ፣ “ማሰሪያ” ይባላል።
* “አሰረ” የሚባለው አንድ ነገር ሲታሰር ወይም ዙሪያውን ሲጠመጠምበት ነው።
* “ማሰሪያ” ማንኛውንም የሚያስር ነገር ይመለከታል። ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ማሰሪያ ከመንቀሳቀስ የሚያግድ ሰንሰለትን፣ ገመድን፣ ጠፍርን ወይም ሌላ ነገርን ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ገመዶች ወይም ሰንሰለቶች እስረኞችን ከግድግዳ ወይም ከወለል ጋር አጣብቆ ለመያዝ ያገለግሉ ነበር።
* “ማሰር” የሚለው ቃል ቁስሉ እንዲፈወስ ለመርዳት ቁስሉን በጨርቅ መጠቅለሉን ለመናገር ያገለግል ነበር።
* የሞተ ሰውን ለቀብር ለማዘጋጀት በጨርቅ “ይታሰር” ወይም ይጠቀለል ነበር።
* “ማሰሪያ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር አንድ ሰው የሚቆጣጠር ወይም ባርያ የሚያደርግ ኃጢአትን የመሳሰሉ ነገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
* ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ በሆነ ሁኔታ ሰዎች እንዲረዳዱ በመካከላቸው ያለው ጥብቅ ግንኙነትም ማሰሪያ ሊባል ይችላል። ይህ በጋብቻ መተሳሰርንም ይመለከታል።
* ለምሳሌ ባልና ሚስት እርስ በርስ፣ “ተሳስረዋል” ወይም ተጣምረዋል። ይህ እግዚአብሔር እንዲላቀቅ የማይፈልገው ትስስር ወይም ጥምረት ነው።
* አንድ ሰው በመሐላ “ይታሰራል”፤ ይህም ማለት የገባውን ቃል፣ “የመፈጸም ግዴታ” አለበት ማለት ነው፥

7
bible/kt/bornagain.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# እንደ ገና መወለድ፣ ከእግዚአብሔር መወለድ፣ አዲስ ልደት
ኢየሱስ፣ “እንደ ገና መወለድ” በሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው እግዚአብሔር አንድን መንፈሳዊ ሙት የሆነ ሰው መንፈሳዊ ሕያው እንዲሆን እንደሚለውጠው ለማመልከት ነበር። “ከእግዚአብሔር መወለድ” ወይም፣ “ከመንፈስ መወለድ” የተሰኙትም ቃሎች አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት የተሰጠውን ሰው ያመለክታሉ።
* ሰዎች ሁሉ መንፈሳዊ ሙታን ሆነው ተወልደዋል፤ ክርስቶስ እንደ አዳኝ ሲቀበሉ ግን፣ “አዲስ ልደት” ይሰጣቸዋል።
* አዲስ መንፈሳዊ ልደት በሚሆነበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አዲሱ አማኝ ውስጥ ለመኖር ይመጣል፤ በሕይወቱ መልካም መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈራ ኃይል ይሰጠዋል።
* አንድ ሰው እንደ ገና እንዲወለድና የእግዚአብሔር ልጅ ማድረግ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።

7
bible/kt/brother.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ወንድም
ብዙውን ጊዜ ወንድም የሚባለው ቢያንስ ከወላጆች ከአንዱ የተወለደ ወንድ ልጅ ነው።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን “ወንድም” የሚለው ቃል የአንድ ጎሳ፣ ነገድ አባሎችን ወይም ሰዎችን የመሳሰሉ ዘመዳሞችን የሚያመለክት አጠቃላይ መጠሪያ ነበር።
* በአዲስ ኪዳን ዘመን ሐዋርያት ወንዶችንም ሆነ ሴቶች አማኞችን ጨምሮ ክርስቲያን ወገኖችን “ወንድም” በማለት ይጠሩ ነበር፤ በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር አባታቸው የሆነ የአንድ መንፈሳዊ ቤተ ሰብ አባሎች ናቸው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያት በተለይ ሴት ስለሆነች ክርስቲያን ሲናገሩ ወይም ወንዶችም ሆነ ሴቶች መካተታቸውን አጽንዖት ለመስጠት ጥቂት ቦታ ላይ፣ “እኅት” በሚል ቃል ተጠቅመዋል። ለምሳሌ ያዕቆብ፣ “ምግብና ልብስ የሌለው ወንድም ወይም እኅት” ሲል እየተናገረ ያለው ስለ አማኞች ሁሉ መሆኑን አጽንዖት ሰጥቷል።

11
bible/kt/call.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,11 @@
# መጥራት፣ ጥሪ፣ ተጠራ፣ መጣራት
“መጥራት” እና “መጣራት” የተሰኙ ቃሎች ቅርብ ላልነበረ ሰው ጮኽ ብሎ አንዳች ነገር መናገር ማለት ነው። ሌሎች ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሏቸው።
* አንድን ሰው “መጣራት” ሩቅ ላለ ሰው ጮኽ ብሎ መናገር ማለት ሲሆን፣ ርዳታ መጠየቅ፣ በተለይም የእግዚአብሔርን ርዳታ መጠየቅ ማለትም ይሆናል።
* ብዙውን ጊዜ መጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጥራት” ሲባል፣ “ና ማለት” ወይም፣ “እንዲመጣ ማዘዝ” ወይም፣ “እንዲመጣ መጠየቅ” ማለት ነው።
* ሕዝቡ እንዲሆኑ ወደ እርሱ እንዲመጡ እግዚአብሔር ሰዎችን ይጣራል። ይህ ለእነርሱ፣ “ጥሪ” ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጠራት” የሚለው ቃል የእርሱ ልጆች እንዲሆኑ፣ በኢየሱስ በኩል የሚገኘውን የመዳን መልእክት የሚናገሩ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ሰዎችን መሾሙን ወይም መምረጡን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
* ይህ ቃል ለአንድ ሰው ስም ማውጣትን በተመለከተም ጥቅም ላይ ይውላል። “ዮሐንስ ተባለ” ሲባል፣ “ዮሐንስ ተብሎ ተጠራ” ወይም “የእርሱ ስም ዮሐንስ ሆነ” ማለት ነው።
* “በአንድ ሰው ስም መጠራት” ማለት ለአንድ ሰው የሌላው ሰው ስም ተሰጠው ማለት ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን በራሱ ስም እንደ ጠራ ይናገራል።
* “በስሜ ጠርቻችኋለሁ” የተሰኘው የተለየ ሐረግ እግዚአብሔር ሰውን በግል በስሙ ያውቀዋል በተለየ ሁኔታም መርጦታል ማለት ነው።

6
bible/kt/centurion.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# መቶ አለቃ
መቶ አለቃ ከእርሱ ሥር 100 ወታደሮች የነበሩት የሮም ሰራዊት ባለ ሥልጣን ነበር።
* ይህን፣ “የመቶ ሰዎች መሪ” ወይም፣ “የወታደሮች መሪ” ወይም፣ “መቶ ሰዎች ላይ ኃላፊነት ያለው ባለ ሥልጣን” በማለት መተርጎም ይቻላል።
* አንድ ሮማዊ ባለ ሥልጣን ወደ ኢየሱስ መጥቶ አገልጋዩን እንዲፈውስለት ለመነው።

12
bible/kt/children.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,12 @@
# ልጆች፣ ልጅ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።
* አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ወይም ተከታዮች፣ “ልጆች” በመባል ተጠርተዋል።
* የአንድን ሰው ዘሮች ለማመልከት፣ “ልጆች” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
* “የ. . .ልጆች” የሚለው ሐረግ የአንድን ነገር ባሕርይ መያዝ ያመለክታል። የሚከተሉት ለዚህ ምሳሌ ይሆናሉ፤
* የብርሃን ልጆች
* የመታዘዝ ልጆች
* የዲያብሎስ ልጆች
ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።

10
bible/kt/christ.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# ክርስቶስ፣ መሲሕ
“መሲሕ” ወይም፣ “ክርስቶስ” የሚለው ቃል፣ “የተቀባ” ማለት ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ነው የሚያመለክተው።
* በሕዝቡ ላይ እንደ ንጉሥ እንዲገዛና ከኃጢአትና ከሞት እንዲያድናቸው እግዚአብሔር የሾመውን የእግዚአብሔር ልጅ ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “መሲሕ” እና “ክርስቶስ” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል፥
* የብሉይ ኪዳን ነቢያት እርሱ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በመቶ በሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ስለ መሲሑ ትንቢት ጽፈዋል።
* የሚመጣውን መሲሕ ለማመልከት፣ “የተቀባ” የሚል ትርጕም ያለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሷል።
* ኢየሱስ ከእነዚህ ትንቢቶች ብዙዎችን ፈጸም፤ እርሱ መሲሕ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተአምራትንም አደረገ፤ የተቀሩት ትንቢቶች የሚፈጸሙት እርሱ እንደ ገና ሲመለስ ነው።
* “እርሱ ክርስቶስ” እና፣ “ክርስቶስ ኢየሱስ” ከተሰኙት ቃሎች መመልከት እንደሚቻለው፣ “ክርስቶስ” የሚለው እንደ መጠሪያ ጥቅም ላይ ውሏል።
* “ኢየሱስ ክርስቶስ” እንደ ተሰኘው፣ “ክርስቶስ” የእርሱም አንድ አካል ሆኗል።

8
bible/kt/christian.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ክርስቲያን
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ ጥቂት ጊዜ በኋላ ስዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ስም አወጡ፤ ክርስቲያን የክርቶስ ተከታይ ማለት ነው።
* የኢየሱስ ተከታዮች ለመጀመሪያ ጊዜ፣ “ክርስቲያኖች” የተባሉት በአንጾኪያ ከተማ ነበር።
* ክርስቲያን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚያምንና ከኃጢአት እንደሚያድነው በእርሱ የሚተማመን ሰው ነው።
* በዘመናችን በእውነት የኢየሱስ ተከታይ ባይሆን እንኳ በክርስቲያን ሃይማኖት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ክርስቲያን” የሚለው እንዲህ ዓይነቱን አይደለም።
* መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ክርስቲያን” ሲል ሁሌም የሚያመለክተው በእውነት በኢየሱስ የሚያምን ሰውን በመሆኑ፣ ክርስቲያን፣ “አማኝ” በመባልም ይታወቃል።

7
bible/kt/church.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ቤተ ክርስቲያን
በአዲስ ኪዳን መሠረት ቤተ ክርስቲያን የሚባለው ለመጸለይና የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ ለመስማት ዘወትር የሚሰበሰቡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነው። “ቤተ ክርስቲያን” ብዙውን ጊዜ፣ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያመለክታል።
* ቃል በቃል የሚያመለክተው ለተለየ ዓላማ በአንድነት የሚሰበሰቡ፣ “ተጠርተው የወጡ” ሰዎችን ጉባኤ ወይም ስብስብን ነው።
* ቃሉ በክርስቶስ አካል ውስጥ በየትኛውም ቦታ ያሉ አማኞችን ሁሉ ለማመልከት ጥቅም ላይ ሲውል ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች በእንግሊዝኛው ቃል መጀመሪያ ላይ ያለውን ፊደል በትልቁ ይጽፋሉ።
* ብዙውን ጊዜ በአንድ ከተማ ውስጥያሉ አማኞች የሚሰበሰቡት በግለ ሰብ ቤት ውስጥ ነበር። እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች የነበሩበት ከተማ ስም ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ፣ “የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን” እንደሚለው።

9
bible/kt/circumcise.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# መገረዝ፣ ግዝረት
“መግረዝ” ከወንድ ወይም ወንድ ከሆነ ትንሽ ልጅ ብልት ትርፍ የሆነውን ቆዳ መቊረጥ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የግርዘት ሥርዓት ሊኖርም ይችላል።
* ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዶን ቤተ ሰብ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድና አገልጋይ እንዲገረዝ እግዚአብሔር አብርሃምን አዝዞት ነበር።
* ቤተ ሰባቸው ውስጥ የሚወለድ ማንኛውንም ወንድ እንዲገርዙ እግዚአብሔር የአብርሃም ዘሮችንም አዝዞአቸዋል።
* “የልብ መገረዝ” የሚለው ሐረግ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ከሰው፣ ኃጢአት “መቆረጥን” ወይም፣ “መወገድን” ያመለክታል።
* በመንፈሳዊ ይዘቱ፣ “የተገረዙ” ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ከኃጢአት ያነጻቸውንና የእርሱ ሕዝብ የሆኑትን ሰዎች ያመለክታል።
* “ያልተገረዙ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የብልት ሥጋቸው ያልተገረዘ ሰዎችን ነው። ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ ያልተገረዙትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸውን ያመለክታል።

8
bible/kt/clean.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ንጽሕ፣ ማንጻት
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ንጹሕ” ምንም ቆሻሻ ወይም እድፍ የሌለበት ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቅዱስ” እና “ከኃጢአት የነጻ” የሚሉትን ለማመልከት በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል።
* “ማንጻት” አንድን ነገር ንጹሕ የማድረግ ሂደት ነው። “ማጠብ” ወይም “ማጽዳት” ተብሎ መተርጎምም ይችላል።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን የትኛው እንስሳ በሥርዓቱ መሠረት “ንጹሕ” የትኛው፣ “ርኵስ” እንደሆነ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ነግሮአቸዋል። ለመብልም ሆነ ለመሥዋዕት የተፈቀዱት ንጹሕ የሆኑ እንስሳት ብቻ ነበሩ። በዚህ ዐውድ መሠረት፣ “ንጹሕ” የተባለው መሥዋዕት እንዲሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ እንስሳ ማለት ነው።
* የቆዳ በሽታ ያለበት ሰው በሽታው ተላላፊ እንዳይሆን ቆዳው እስኪፈወስ ድረስ፣ እንደ ርኵስ ይቆጠር ነበር። ሰውየው እንደገና “ንጹሕ” እንዲባል ከተፈለገ ከቆዳ በሽታ ለመንጻት ሊታዘዛቸው የመገቡ መመሪያዎች ነበሩ።
* አንዳንዴ፣ “ንጽሕ” የሚለው ቃል ግበረ ገባዊ ንጽሕናን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

6
bible/kt/command.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ማዘዝ፣ ትእዛዝ
ማዘዝ ማለት አንዳች ነገርን እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች መናገር ማለት ነው። ትእዛዝ የሚባለው እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች የተሰጠው መመሪያ ነው።
* ምንም እንኳ እነዚህ ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ “ትእዛዝ” የሚለው ቃል የበለጠ መድበኛና ቋሚ የሆኑ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያመለክታል፤ ለምሳሌ “አሥሩ ትእዛዞች።”
* አንድ ትእዛዝ አዎንታዊ (ለምሳሌ፣ “ወዳጆችን አክብር”) ወይም አሉታዊ፣ (ለምሳሌ፣ “አትስረቅ”) ሊሆን ይችላል።

7
bible/kt/compassion.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ርኅራኄ፣ ርኅሩኅ
“ርኅራኄ” ለሰዎች ማሰብ፣ አተለይም መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች እነርሱ ቦታ ሆኖ ስሜታቸውን መጋራትን ያመለክታል። “ርኅሩኅ” ሰው ለሌሎች ሰዎች ያስባል እነርሱንም ይረዳል።
* ብዙውን ጊዜ፣ “ርኅራኄ” የሚለው ቃል ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግንና እነርሱን ለመርዳት አንዳች ነገር ማድረግንም ይጨምራል።
* እግዚአብሔር ርኅሩኅ መሆኑን ያም ማለት እርሱ ፍቅርንና ምሕረትን የተሞላ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
* ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ፣ “ርኅራኄን ልበሱ” በማለት ይመክራቸዋል። ለሰዎች የሚያስቡና የሚጠነቀቁ እንዲሆኑና ችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ንቁዎች እንዲሆኑ ያስስባቸዋል።

7
bible/kt/condemn.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# መኮነን፣ ኵነኔ
“መኮነን” እና “ኵነኔ” አንዳች በደል ከመፈጸሙ የተነሣ ሌላው ላይ መፍረድን ያመለክታል።
* “መኮነን” ካደረገው ጥፋት የተነጃ ያንን ሰው መቅጣትንም ይጨምራል።
* አንዳንዴ፣ “መኮነን” የሚለው በሐሰት ሰውን መክሰስ ወይም ያልተመጣጠነ ፍርድ መስጠት ማለት ሊሆን ይችላል።
* “ኵነኔ” ሰውን የመኮነን ወይም የመክሰስ ተግባር ነው።

9
bible/kt/confess.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# መመስከር፣ ምስክርነት
መመስከር አንድ ነገር እውነት መሆኑን መቀበል ወይም መናገር ማለት ነው። “ምስክርነት” አንድ ነገር እውነት መሆኑን በቃል ወይም በጽሑፍ በዚያም መስማማት ማለት ነው።
* “መመስከር”እግዚአብሔርን በተመለከተ በድፍረት እውነቱን መናገርን ያመለክታል። ኃጢአት መሥራታችንን መቀበልንም ያመለክታል።
* ሰዎች ኃጢአት መሥራታቸውን ሲናዘዙ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
* አማኞች እርስ በርሳቸው ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ መንፈሳዊ ፈውስ እንደሚኖር ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ ጽፎአል።
* አንድ ቀን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ሰዎች ሁሉ እንደሚመሰክሩ ወይም እንደሚናገሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ጽፎአል።
* ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ካመኑና እግዚአብሔርንም ከሙታን እንዳስነሣው ሰዎች ከመሰከሩ እንደሚድኑ ጳውሎስ ይናገራል።

9
bible/kt/conscience.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# ኅሊና
ኅሊና አንድ ሰው ኃጢአት እያደረገ መሆኑን እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያሳውቅበት የሰውየው አስተሳሰብ አንድ ክፍል ነው።
* ትክክል የሆነውንና ስሕተት የሆነውን ለይተው ማወቅ እንዲረዳቸው እግዚአብሔር ለሰዎች ኅሊና ሰጥቷል።
* ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሰው፣ “ንጹሕ” ወይም፣ “ያልቆሸሸ” ኅሊና አለው ይባላል።
* አንድ ሰው፣ “ንጹሕ ኅሊና” አለው ከተባለ በውስጡ ምንም የተደበቀ ኃጢአት የለም ማለት ነው።
* ሰዎች ኅሊናን ችላ ካሉና ኃጢአት ሲያደርጉ በደለኝነት የማይሰማቸው ከሆነ፣ ኃጢአትን በተመለከተ ኅሊናቸው ንቁ አይደለም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በጋለ ብረት የመተኮስን ያህል፣ “የደነዘዙ” ኅሊና ይለዋል። እንዲህ ያለው ኅሊና፣ “የሞተ” ወይም፣ “የተበከለ” ሊባል ይችላል።
* ይህን ቃል፣ “ውስጣዊ ግብረ ገብ መሪ”፣ “ግብረ ገባዊ አስተሳሰብ” ማለት ይቻላል።

8
bible/kt/consecrate.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# መለየት
መለየት አንድን ነገር ወይም ሰው እግዚአብሔርን እንዲያገለግል መመደብ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የተለየ ሰው ወይም እቃ ለእግዚአብሔር እንደ ተቀደሰና እንደ ተለየ ይቆጠራል።
* የዚህ ቃል ትርጕም፣ “መቀደስ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ሥርዓት ባለው መልኩ አንድን ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት መለየት የሚለውንም ይጨምራል።
* ለእግዚአብሔር የተለየ ነገሮች የመሥዋዕት እንስሳትን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያንና መገናኛው ድንኳንን ወይም ቤተ መቅደሱንም ይጨምራሉ።
* ለእግዚአብሔር የተለዩ ሰዎች ካህናትን፣ የእስራኤል ሕዝብንና ያደጉ ወንድ ልጆችን ይጨምራል።
* እንደነጹና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ሰዎችን ወይም ነገሮችን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጁ ማድረግን ከሆነ፣ “መለየት” የሚለው ቃል አንዳንዴ፣ “ማንጻት” ከተሰኘው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ይኖረዋል።

8
bible/kt/cornerstone.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# የማእዘን ድንጋይ
“የማእዘን ድንጋይ” የሚለው ሐረግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ተጠርቦ የሕንጻው መሠረት አንድ ጥግ ላይ የሚቀመጥ ትልቅ ድንጋይ ነው።
* ሌሎች ድንጋዮች ሁሉ የሚለኩትና የሚቀመጡት ከማእዘን ድንጋይ መሠረት ነው።
* የማእዘን ድንጋይ ሕንፃው በሙሉ ጥንካሬና ዘላቂነት እንዲኖረው በጣም አስፈላጊ ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የማእዘን ድንጋይ” ሲባል አማኞች ደግሞ ሕያዋን ድንጋዮች ተብለዋል።
* የማእዘን ድንጋይ ሕንፃውን ደግፎ እንደሚይዝና የሕንፃውን ትክክለኛነት እንደሚወሰን ሁሉ አማኞች የተመሠረቱትና የተደገፉት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።

10
bible/kt/covenant.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# ኪዳን
ኪዳን አንዱ ወይም ሁለቱም የሚፈጽሙት በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ መደበኛ አሳሪ ስምምነት ነው።
* ስምምነቱ በሁለት ግለ ሰቦች፣ ሕዝቦች፣ ወይም በእግዚአብሔርና በሕዝብ መካከል ሊደረግ
* ሰዎች እርስ በርስ ኪዳን ካደረጉ አንድ ነገር ለማድረግ ቃል ይገባሉ፤ ያንንም ማድረግ አለባቸው።
* በሰዎች መካከል ለሚደረግ ኪዳን ምሳሌ የሚሆኑን የጋብቻ ኪዳን፣ የሥራ ስምምነትና በአገሮች መካከል የሚደረጉ ውሎች ናቸው ።
* ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በርካታ ኪዳኖች አድርጎ ነበር።
* በአንዳንድ ኪዳኖች ውስጥ የእርሱን ድርሻ ለመፈጸም እግዚአብሔር ቃል የገባው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነበር። ለምሳሌ ዓለምን ሁሉ በማያዳርስ ጎርፍ ከእንግዲህ ምድርን እንደማያጠፋ እግዚአብሔር ቃል ከሰው ልጅ ጋር ኪዳን ያደረገው ሰው ማሟላት የነበረበት ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳይኖር ነው።
* በሌሎች ኪዳኖች የእርሱን ድርሻ እንደሚፈጽም እግዚአብሔር ቃል የገባው ሰዎች ከታዘዙትና የኪዳኑን የእነርሱን ድርሻ ከፈጸሙ ብቻ ነበር።

View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ለኪዳኑ ታማኝ፣ ለኪዳኑ እውነተኛ
ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝ መሆኑን ነው።
* “ኪዳን” በተሰኘ ውል ያለው ስምምነት መሠረት እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ተስፋ ሰጠ።
* ያህዌ፣ “ለኪዳኑ ታማኝ” ወይም፣ “ለኪዳኑ እውነተኛ” መሆኑ የሚያመለክተው እርሱ ለሕዝቡ የገባውን ቃል የሚጠብቅ መሆኑን ነው።
* የኪዳኑን ተስፋ ለመጠበቅ እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑ እርሱ ለሕዝቡ ያለው ተስፋ መገለጫ ነው።
* “እውነተኛ” የሚለው የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝና መሆኑን የሚያመለክት ሌላ ቃል ነው።

6
bible/kt/cross.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# መስቀል
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን መስቀል አንድ ቀጥ ብሎ የወጣ እንጨት ሲሆን ጫፉ አካባቢ አንድ ሌላ ግንድ ይጋደምበት ነበር።
* በሮም መንግሥታት ዘመን አንድ ሮማዊ ባለ ሥልጣን መስቀል ላይ በመቸንከር ወይም መስቀል ላይ በማሰርና እዚያ እንዲሞቱ በማድረግ ወንጀለኞችን ይቀጣ ነበር።
* ኢየሱስ ባልፈጸመው ወንጀል በሐሰት ተከሰሰ፤ ሮማውያንም መስቀል ላይ ገደሉት።

7
bible/kt/crucify.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# መስቀል (ሰውን)
“መስቀል” ማለት አንድን ሰው መስቀል ላይ ማሰርና በታላቅ ሕመምና ስቃይ እስኪሞት ድረስ እዚያው መተው ማለት ነው።
* የሚሰቀለው ሰው መስቀሉ ላይ ይታሰር ወይም ይቸነከር ነበር። በዚህ መልኩ የሚሰቀሉ ሰዎች በከባድ ደም መፍሰስ ወይም በመታረን ይሞቱ ነበር።
* አደገኛ ወንጀለኞችን ወይም በሮም መንግሥት ላይ ያመፁ ሰዎችን ለመግደል ሮማውያን በእንደዚህ ዐይነቱ ቅጣት ይጠቀሙ ነበር።
* የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን እንዲሰቅሉ ወታደሮቹ እንዲያዝ ሮማውያን ባለ ሥልጣን ጠየቁ። ወታደሮቹ ኢየሱስን መስቀል ላይ ቸነከሩ። እኢያ ላይ ስድስት ሰዓት ያህል ተሰቃይቶ ሞተ።

7
bible/kt/curse.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# መርገም፣ የተረገመ
“መርገም” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ላይ መጥፎ ነገር እንዲደርስበት ማድረግ ነው።
* አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ላይ ጉዳት እንዲደርስ መናገር መርገም ነው።
* ሰውን መርገም እዚያ ሰው ላይ መጥፎ ነገር እንዲደርስበት የመፈለግ መገለጫ ሊሆን ይችላል።
* ቅጣትን አንድ ሰው ሌላው ላይ የሚያደርሰው ሌላ አሉታዊ ነገርን ሊያመለክትም ይችላል።

View File

@ -0,0 +1,7 @@
# የጽዮን ሴት ልጅ
የጽዮን ሴት ልጅ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ብዙውን ጊዜ ትንቢት ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “ጽዮን” የኢየሩሳሌም ከተማ ሌላ ስም ነበር።
* “ጽዮን” እና፣ “ኢየሩሳሌም” እስራኤልን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላሉ።
* “ሴት ልጅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ውድ ምሆንን ወይም ፍቅርን የሚያመለክት ሐረግ ነው። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ላለው ትዕግሥትና ጥንቃቄ ተለዋጭ ዘይቤ ነው።

8
bible/kt/dayofthelord.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# የጌታ ቀን፣ ይያህዌ ቀን
“የያህዌ ቀን” የተሰኘው የብሉይ ኪዳን አገላለጽ ከኀጢአታቸው የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚቀጣበትን የተለየ ቀን ወይም ቀኖች ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
* “የጌታ ቀን” የሚለው የአዲስ ኪዳን አገላለጽ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው በመጨረሻው ቀን ጌታ ኢየሱስ በሰዎች ለመፍረድ ተመልሶ የሚመጣበትን ቀን ነው።
* ይህ ወደ ፊት የሚመጣው የመጨረሻ ፍርድና ትንሣኤ አንዳንድ ጊዜ፣ “የመጨረሻው ቀን” ተብሎ ይጠራል። ይህ ጊዜ የሚጀምረው በኀጢአተኞች ለመፍረድና ለዘላለም መንግሥቱን ለመምሥረት ጌታ ኢየሱስ ሲመታ ነው።
* እነዚህ ሐረጎች ውስጥ፣ “ቀን” የሚለው ቃል አንዳንዴ ቃል በቃል “ጊዜን” ወይም ከቀን የረዘመ “ወቅትን” ሊያመለክት ይችላል።
* የቅጣቱ ቀን አንዳንዴ፣ “የእግዚአብሔር ቍጣ መፍሰስ” ተብሎ ይጠራል።

8
bible/kt/deacon.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ዲያቆን
ዲያቆን ምግብን ወይም ገንዘብን በመሳሰሉ ተግባራዊ ነገሮች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን በመርዳት የሚያገለግል ሰው ነው።
* “ዲያቆን” የሚለው ቃል በቀጥታ የተወሰደው “ባርያ” ወይም “አገልጋይ” የሚል ትርጕም ካለው ግሪክ ቃል ነው።
* የጥንት ክርስቲያኖች ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ዲያቆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ያለው የአገልግሎት ዘርፍ ነው።
* ለምሳሌ ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ መበለቶችና ድኾች ገንዘብና ምግብ በአግባቡ መዳረሱን የሚያጣሩ ዲያቆናት ነበሩ።
* “ዲያቆን” የተሰኘው ቃል፣ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ” ወይም፣ “የቤተ ክርስቲያን ሠራተኛ” ተብሎ ሊተረጎም ወይም የአጥቢያው ክርስቲያን ማኅበረ ሰብን የሚጠቅም ተግባር እንዲፈጽም በሥርዐት መሾምን በሚያሳይ ሌላ ሐረግ ወይም ቃል መጠቀም ይችላል።

8
bible/kt/demon.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ጋኔን፣ ክፉ መንፈስ፣ ርኵሳን መናፍስት
እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት አጋንንትን ሲሆን፣ አጋንንት የእግዚአብሔርን ፈቀድ የሚቀወሙ መንፈሳዊ ፍጥረቶች ናቸው።
* እርሱን እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ። ዲያብሎስ በእግዚአብሔር ላይ ሲያምጽ ከመላእክቱም ጥቂቶቹ በማመጻቸው ከሰማይ ተጣሉ። አጋንንትና ክፉ መናፍስት፣ “እነዚህ የተጣሉ” መላእክት እንደ ሆኑ ይታሰባል።
* እነዚህ አጋንንት አንዳንዴ፣ “ርኵሳን መናፍስት” ተብለው ይጠራሉ። “ርኵስ” “ንጹሕ ያልሆነ” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “ቅዱስ ያልሆነ” ማለት ነው።
* አጋንንት የሚያገለግሉት ዲያብሎስን ስለ ሆነ ክፉ ነገር ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜ እነርሱ ውስጥ በመግባት ሰዎችን ይቆጣጠራሉ።
* አጋንንት ከሰው የበለጠ ብርቱ ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔርን ያህል ግን ብርቱ አይደሉም።

View File

@ -0,0 +1,6 @@
# አጋንንት ያደሩበት
አጋንንት ያደሩበት ሰው የሚያደርገውንና የሚያስበውን የሚቆጣጠሩ አጋንንት ወይም ክፉ መናፍሳት ውስጥ ይኖራሉ።
* አጋንንት ያደሩበት ሰው ብዙ ጊዜ ራሱን ወይም ሌሎችን ይጎዳል፤ እንደዚያ የሚያስደርጉት ውስጡ ያሉት አጋንንት ናቸው።
* ከውስጣቸው አጋንንቱ እንዲወጡ በማዘዝ ኢየሱስ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎችን ነጻ አውጥቶአል። ብዙ ጊዜ ይህ፣ “አጋንንትን ማስወጣት” የሚባለው ነው።

11
bible/kt/disciple.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,11 @@
# ደቀ መዝሙር
“ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው።
* ትምህርቱን በመስማትና ለእርሱ በመታዘዝ በየሄደበት ሁሉ ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች፣ “ደቀ መዛሙርት” ይባላሉ።
* መጥምቁ ዮሐንስም የራሱ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
* ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን እርሱን የተከተለና ትምህርቶቹን ያደመጡ ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
* የቅርብ ተከታዮቹ እንዲሆኑ ኢየሱስ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት መረጠ፤ እነዚህም የእርሱ “ሐዋርያት” የተባሉት ናቸው።
* አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት፣ “ደቀ መዛሙርት” ወይም፣ “አሥራ ሁለቱ” በሚል ስያሜ መጠራታቸው ቀጥሎአል።
* ወደ ሰማይ ከመሄዱ ጥቂት ቀደም ሲል የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ደቀ መዝሙርቱን አዝዞአል።
* በኢየሱስ የሚያምንና ለእርሱ ትምህርት የሚታዘዝ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል።

7
bible/kt/discipline.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ሥርዓት፥ ራስን መግዛት ወይም ራስን በሥርዓት መምራት
“ሥርዓት” ለተወሰኑ ግብረ ገባዊ መመሪያዎች እንዲታዘዙ ሰዎችን መሠልጠንን ነው የሚያመለክተው።
* ግብረ ገባዊ መመሪያዎችንና አቅጣጫዎችን በመስጠትና እንዲታዘዙ በማስተማር ወላጆች ልጆቻቸውን ሥርዓት ያስይዛሉ።
* በተመሳሳይ መንገድ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖራቸውና እንደ ደስታ፣ ትዕግሥትን የመሳሰሉ ፍሬዎች እንዲያፈሩ እግዚአብሔርም ልጆቹን ሥርዓት ያስይዛል።
* ሥርዓት ሲባል እግዚአብሔርን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚቻል መመሪያን እንደሚያመለክት ሁሉ፣ ከእርሱ ፈቀድ ውጪ የሆኑትን መቅጣትንም ያካትታል።

3
bible/kt/divine.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
# መለኮት
መለኮት የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር የሆነ ማንኛውንም ነገር ይመለከታል። ይህ ቃል ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ “መለኮታዊ ሥልጣን”፣ “መለኮታዊ ፍርድ”፣ “መለኮታዊ ባሕርይ”፣ “መለኮታዊ ኃይል” እና፣ “መለኮታዊ ክብር የተሰኙት ናቸው።

7
bible/kt/dominion.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ግዛት
ግዛት ሰዎችን፣ እንስሳትንና መሬትን የመቆጣጠር፣ የመግዛት ኃይልና ሥልጣንን ያመለክታል።
* ነቢይ፣ ካህንና ንጉሥ በመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን ሁሉ እንደሚገዛ ተነግሮአል።
* በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ ሞት የሰይጣን ግዛት ለዘላለም ተሸንፎአል።
* በፍጥረት ጊዜ ሰው የባሕር ዓሦችን፣ በአየር የሚበሩ ወፎችንና ምድር ላይ የሚኖሩ ፍጥረቶችን ሁሉ እንዲገዛ እግዚአብሔር ተናገረ።

6
bible/kt/elect.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# የተመረጠ፣ የተመረጠ ሕዝብ፣ የተመረጠው፣ ምርጦች
“የተመረጠ” ወይም፣ “ምርጦች” የሚለው ቃል በቃል፣ “የተመረጡት” ወይም፣ “የተመረጠ ሕዝብ” ማለት ሲሆን አባባሉ የእርሱ ሕዝብ እንደሆኑ እግዚአብሔር የመደባቸውን ወይም የመረጣቸውን ያመልክታል። “የተመረጡ” ወይም፣ “በእግዚአብሔር የተመረጠው፣ የተመረጠ መሲሕ የሆነው የኢየሱስ መጠሪያ ነው።
* እግዚአብሔር እንዲቀደሱ፣ መልካም መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈሩ እግዚአብሔር ሰዎችን መረጠ። “የተመረጠ” የሚለው ቃል የሕዝቡ መሪ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የመደባቸውን ሙሴንና ንጉሥ ዳዊትን የመሳሰሉ ሰዎች ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። እንደ እግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ የእስራኤልን ሕዝብም ያመለክታል።
* “ምርጦች” የተሰኘው ጥንታዊ ሐረግ ቃል በቃል፣ “የተመረጡት” ወይም፣ “የተመረጠ ሕዝብ” ማለት ነው።

8
bible/kt/ephod.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ኤፉድ
ኤፉድ እስራኤላውያን ካህናት ይለብሱት የነበረ መጎናጸፊያ ዐይነት ጨርቅ ነው። ትከሻ ላይ የሚገናኙ የፊትና የኋላ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት፤ ከዚያም በጨርቅ መታጠቂያ ወገብ ላይ ይታሰር ነበር።
* አንዱ አይነት ኤፉድ ከተራ ተልባ እግር የሚሠራ ሲሆን፣ የሚለብሱትም ተራ ካህናት ነበሩ።
* ሊቀ ካህኑ የሚለብሰው ኤፉድ በወርቅ ያጌጠና በሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ጥልፍ የተሠራ ነበር።
* የሊቀ ካህኑ ደረት ልብስ ከኤፉዱ ፉት ለፊት አካል ጋር ይያያዛል፣ ከደረት ልብሱ በስተጀርባ አንድን ጉዳይ አመልክቶ የእርሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚጠይቅባቸው የከበሩ ድንጋዮች ኡሪምና ቱሚም ይቀመጣሉ።
* መሳፍንቱ ጌዴዎን በስሕተት ከወርቅ የሠራውን ኤፉድ እስራኤላውያን እንደ ጣዖት ሲያመልኩት ነበር።

8
bible/kt/eternity.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ዘላለም፣ ዘላለማዊ
“ዘላለም” እና “ዘላለማዊ” በጣም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ የሚያመለክቱት ሁሌም የሚኖር ወይም ማለቂያ ማብቂያ የሌለውን ነገር ወይም ሁኔታ ነው።
* “ዘላለም” ጅማሬም ሆነ ፍጻሜ የሌለውን ሁኔታ ያመለክታል። ማለቂያ፣ ማብቂያ የሌለው ሕይወትንም ያመለክታል።
* ከዚህ የአሁን ሕይወት በኋላ የሰው ልጆች በመንግሥተ ሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከእግዚአብሔር ተለይተው በገሃነም ዘላለምን ያሳልፋሉ።
* ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማይ መኖርን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ “ዘላለማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
* “ከዘላለም እስከ ዘላለም” የሚለው ሐረግ ማለቂያ የሌለውን ጊዜ የሚያመለክት ሲሆን፣ ዘላለም ወይም የዘላለም ሕይወት ምን ማለት መሆኑን ይገልጻል።

7
bible/kt/eunuch.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ጃንደረባ
ብዙ ጊዜ፣ “ጃንደረባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተኮላሸ ወንድን ነው በኋላ ግን ቃሉ አካላዊ ጉድለት ባይኖርባቸውም በአጠቃላይ ማንኛውንም የመንግሥት ባለሥልጣን የሚያመለክት ሆነ።
* ብልታቸው በመጎዳቱ ወይም የግብረሥጋ ግንኙነት ማድረግ ባለመቻሉ፣ አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው እንደሚወለዱ ኢየሱስ ተናግሯል። አንዳንዶች ደግሞ በድንግልና እንደጃንደረባ መኖርን መርጠዋል።
* በጥንት ዘመን ጃንደረቦች ብዙ ጊዜ የነገሥታቱን ሴቶች እንዲጠብቁ ቤተመንግሥት ውስጥ ያገለግሉ ነበር (ከነአስቴር ታሪክ መመልከት ይቻላል)
* አንዳንድ ጃንደረቦች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ፤ ይህን በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሰው ፊልጶስ ወንጌል ከሰበከለት ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ማየት ይቻላል።

8
bible/kt/evangelism.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ወንጌላዊ
“ወንጌላዊ” የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች(ወንጌል) ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው።
* የ “ወንጌላዊ” ቃል በቃል ትርጉም፣ “የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች የሚሰብክ ሰው ማለት ነው።”
* በኢየሱስና መስቀል ላይ በከፈለው የኀጢአት መሥዋዕት በማመን የእግዚአብሔር መንግሥት አካል እንደሚሆኑ ለሰዎች የምሥራቹን እንዲናገሩ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ላከ።
* ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን የምሥራች እንዲያካፍሉ ተነግሯቸዋል።
* አንዳንድ ክርስቲያኖች ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ወንጌልን ለሌሎች የማካፈል ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ ታድለዋል። እንዲህ ያሉ ሰዎች ወንጌል የማዳረስ ስጦታ አላቸው፤ “ወንጌላዊ” ተብለውም ይጠራሉ።

7
bible/kt/evil.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ክፉ፣ ዐመጽ(ዐመጸኛ)፣ ዐመጻ
“ክፉ” እና “ዐመጸኛ” የተሰኙት ቃሎች ሁለቱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባሕርይና ፈቃድ የሚቃወም ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ።
* “ክፉ” የሚለው ቃል የሰውን ፀባይ የሚያመለክት ሲሆን፣ “ዐመጸኛ” የሚለው ደግሞ የሰውን ባሕርይ ሊያመለክት ይችላል። ይሁን እንጂ፣ የሁለቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው።
* “ዐመጻ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ዐመጽ ሲያደርጉ የሚኖረውን ሁኔታ ነው።
* ሰዎች ሌሎችን በመግደል፣ በመስረቅ፣ ስም በማጥፋት ወይም በሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር የክፋትን ወይም የዐመጻን ውጤት በግልጽ ማየት ይቻላል።

6
bible/kt/exalt.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ከፍ ማድረግ፣ ከፍታ
ከፍ ማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ማመስገንና ማክበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ማድረስንም ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን ከፍ ለማድረግ ነው።
* አንድ ሰው ራሱን ከፍ ካደረግ፣ ስለራሱ በትዕቢትና በእብሪት እያሰበ ነው ማለት ነው።

6
bible/kt/exhort.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ማበረታታት
“ማበረታታት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ትክክልና እውነት የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ማደፋፈርን ነው።
* የማበረታታቱ ዓላማ ሰዎች ከኀጢአት እንዲርቁና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያደርጉ መምከር ነው።
* ክርስቲያኖች እርስ በርስ እንዲበረታቱና፣ ክፉ ቃል እንዳይመለለሱ አዲስ ኪዳን ያስተምራል።

9
bible/kt/faith.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# እምነት
በአጠቃላይ ደረጃ “እምነት” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር፣ በሰው ወይም፣ በነገሮች መተማመንን፣ መደገፍን፣ ወይም፣ መመካትን ነው።
* “ማመን” ማለት የምናምነው ሰው የሚናገረውና የሚያደርገው ሁሉ እውነትና አስተማማኝ መሆኑን በሙሉ ልብ መቀበል ማለት ነው።
* “በኢየሱስ ማመን” ኢየሱስን በተመለከተ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ሁሉ ማመን ማለት ነው። በተለይም በኢየሱስና ሰዎችን ከኅጢአታቸው እንደሚያነጻቸው ከኅጢአታቸው የተነሳ ከሚጠብቃቸው ቅጣት እንደሚያድናቸው ማመን ማለት ነው።
* አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ካመነ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ውስጥ ስለሚኖር መልካም መንፈሳዊ ፍሬ ወይም የሕይወት ለውጥ ይኖረዋል።
* አንዳንድ፣ “እምነት” “የእምነት እውነት” በሚለው በተገለጸው መሠረት፣ በአጠቃላይ ስለ ኢየሱስ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ያመለክታል።
* “እምነትን መጠበቅ” ወይም፣ “እምነትን መተው” በሚለው ዐውድ ውስጥ “እውነት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን በተመለከተ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ማመንን ነው።

7
bible/kt/faithful.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ታማኝ፣ ታማኝነት
ለእግዚአብሔር፣ “ታማኝ” መሆን ዘወትር በእርሱ ትምህርት መኖር ማለት ነው። ለእርሱ በመታዘዝ እውነተኛነትን ማሳየት ማለት ነው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ “ታማኝነት” ይባላል።
* ታማኝ የሆነ ሰው ሁሌም ቃሉን እንደሚጠብቅና ለሌሎች ያለበትን ኅላፊነት ሁሌም እንደሚወጣ እምነት ሊጣልበት ይችላል።
* ታማኝ ሰው ረጅምና አስቸጋሪ ቢሆንበት እንኳ በጀመረው ሥራ ይተጋል።
* ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ዘወትር እግዚአብሔር እንድናደርግ የፈለገውን በማድረግ መጽናት ነው።

7
bible/kt/faithless.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# እምነት የለሽ እምነት ወይም የሚተማመንበት የሌለው ማለት ነው።
እምነት የለሽ፣ እምነት የለሽነት
* ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለው በእግዚአብሔር የማያምኑና ይህንንም በክፉ አኗኗራቸው ያሚያሳዩ ሰዎችን ለማመልከት ነው።
* ነብዩ ኤርምያስ እምነት የለሽ በመሆናቸውና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው እስራኤልን ይወቅሳል።
* ጣዖቶችን አመለኩ፤ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ወይም ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ሰዎችን መጥፎ ባሕል ተከተሉ።

10
bible/kt/falsegod.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# ሐሰተኛ አምላክ፣ ባዕድ አምላክ፣ ጣዖት
ሐሰተኛ አምላክ በአንዱ እውነተኛ አምላክ ቦታ ሰዎች የሚያመልኩት ነገር ነው። ወንድ ጣዖት እንዳለ ሁሉ ሴት ጥዖትም አለች።
* ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ እውነተኛ አምላክ ያህዌ ብቻ ነው።
* አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውን የሚወክልላቸው ምስል ይሠራሉ።
* ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ሕዝብ ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ በተደጋጋሚ ለእርሱ ከመታዘዝ ወደኋላ ሄደው እንደነበር እናያለን።
* የሚያመልኳቸው ሐሰተኛ አማልክትና ጣዖቶች ኅይል እንዳላቸው እንዲያምኑ ብዙውን ጊዜ አጋንንት ሰዎችን ያሳስታሉ።
* በኣል፣ ዳጎንና ሞሎክ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ብዙ ሐሰተኛ አማልክት መከከል ሦስቱ ናቸው።
* አሼራና አርጤምስ(ዳያና) የጥንት ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ሴት አማልክት ሁለቱ ነበሩ።

8
bible/kt/favor.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ሞገስ፣ ሞገስ ያለው፣ አድልዎ (ከሌሎች የተለየ ሞገስ የሚደረግለት)
ሞገስ እርሱን በተመለከተ ጥሩ አመለካከት ያለንን ሰው ለመጥቀም የሚደረግ ነገርን ያመለክታለ። “ሞገስ ያለው” ነገር ቀና ተቀባይነት ያለው ወይም ጠቃሚ ነው።
* “አድልዎ” ለአንዱ ሞገስ ማሳየት ለሌላው ግን ሞገስ መንፈግ ነው። አንዳንዴ ሰዎች ሀብታም ወይ ታዋቂ በመሆናቸው ብቻ ከሌላው የተለየ ሞገስ (አድልዎ) ይደረግላቸዋል።
* ኢየሱስ፣ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት፣ “ሞገስ በማግኘት አደገ።” ይህም ፀባይና ባሕርዩ በእነርሱ ዘንድ ተቀባይነት ነበረው ማለት ነው።
* “ሞገስ አገኘ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር በሌሎች ዘንድ መወደድን ተቀባይነት ማግኘትን ያመልክታል።
* አንድ ንጉሥ ለሰው ሞገስ አደረገ ማለት ያ ሰው ያቀረበው ልመና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ ማለት ነው።

7
bible/kt/fear.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ፍርሃት፣ ፈራ፣ የያህዌ ፍርሃት
“ፍርሃት” እና፣ “ፈራ” የሚሉት በእርሱ ወይም በሌሎች ላይ ጉዳት ይመጣል ብሎ ሲያስብ የሚኖረው ደስ የማይል ስሜት ነው።
* “ፍርሃት” ሥልጣን ላለው ሰው ጥልቅ አክብሮት መገለጫ ሊሆንም ይችላል።
* “የያህዌ ፍርሃት” (ወይም በተለመደው መልኩ፣ “የእግዚአብሔር ፍርሃት” እና፣ “የጌታ ፍርሃት”) ከልብ እግዚአብሔርን ማክበርንና ያንን በመታዘዝ ማሳየትን ያመለክታል። ይህ ዐይነቱ ፍርሃት እግዚአብሔር ቅዱስና ኀጢአትን የሚጠላ መሆኑን ከመገንዘብ የሚመጣ ነው።
* ያህዌን የሚፈራ ሰው ጠቢብ (አስተዋይ) እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

8
bible/kt/fellowship.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ኅብረት
አጠቃላይ በሆነ ደረጃ፣ “ኅብረት” ተመሳሳይ ፍላጎትና ልምምድ ያላቸው የአንድ ማኅበር አባሎች መካከል የሚደረግ የወዳጅነት ግንኙነትን ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ኅብረት” በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች አድነትን ነው ምንጊዜም የሚያመለክተው።
* ክርስቲያናዊ ኅብረት ከክርስቶስና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት አመካይነት አማኞች እርስበርስ ያላቸውን ግንኙነት የሚገልጹበት መንገድ ነው።
* የጥንት ክርስቲያኖች ኅብረታቸውን የሚገልጹት የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት በመካፈል፣ በአንድነት በመጸለይ ያላቸውን ሁሉ በመካፈልና አብረው በመመገብ ነበር።
* ክርስቲያኖች በኢየሱስ፣ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን መለያየት ባስወገደበት የመስቃል ላይ መሥዋዕታዊ ሞቱ በማመናቸው ከእግዚአብሔርም ጋር ኅብረት አላቸው።

6
bible/kt/filled.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# በመንፈስ መሞላት
“በመንፈስ ቅዱስ መሞላት” የሚለው አገላለጽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማድረግ እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ለሰው የሚሰጠውን ኅይል የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።
* “መሞላት” የሚለው ፈሊጣዊ ቃል በዙውን ጊዜ “በቁጥጥር ሥር መሆን” ማለት ነው።
* የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ሲከተሉና እግዚአሔር የሚፈልገውን ለማድረግ እንዲረዳቸው ሙሉ በሙሉ በእርሱ ሲተማመኑ ሰዎች፣ “በመንፈስ ይሞላሉ”።

8
bible/kt/flesh.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ሥጋ
መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
* የሰው ልጆችን ወይም ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋ” የሚለውን በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል።
* አዲስ ኪዳን፣ “ሥጋ” ኅጢአተኛውን የሰዎች ባሕርይ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
* “የሥጋ ቁራጭ፣ የአጥንት ፍላጭ” የሚለው ፈሊጣዊ ቋንቋ በሥጋ የምንዛመደውን ሰው ማለት አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ የልጅ ልጆችን፣ እኅት፣ ወንድሞችንና ሌሎችን የቅርብ ዘመዶችን ያመለክታል።
* “ሥጋና ደም” የአንድ ሰው የቀደሙ አባቶችንና እናቶችንም ያመለክታል።

8
bible/kt/foolish.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ሞኝ፣ ሞኝነት፣ ከንቱነት
“ሞኝ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ምርጫ የሚያደርግ በተለይም አለመታዘዝን የሚመርጥ ሰው ነው። “ሞኝነት” ማስተዋል የሌለው ሰው ወይም ፀባይ የሚገለጥበት መንገድ ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ሞኝ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የማያምንና ለእርሱ የማይታዘዝ ሰውን ነው። ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው በእግዚአብሔር ከሚያምንናን ለእርሱ ከሚታዘዝ ሰው አንጻር ነው።
* መዝሙሮቹ ውስጥ ዳዊት በእግዚአብሔር የማያምንና በእግዚአብሔር ፍጥረቶች ውስጥ ያሉትን ማስረጃዎች ችላ የሚልን ሰው ሞኝ በማለት ይጠራዋል።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፍ ምሳሌ ሞኝ ሰው ምን ማለት እንደ ሆነ ብዙ መገለጫዎች ያቀርባል።
* “ከንቱነት” ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ በመሆኑ ማስተዋል የሌለበት ድርጊት ያመለክታል።

8
bible/kt/forgive.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ይቅር ማለት ይቅርታ
አንድን ሰው ይቅር ማለት ከዚህ ቀደም ባደረገው መጥፎ ነገር ቂም አለመያ ማለት ነው። “ይቅርታ” ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ነው።
* ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ይቅር ማለት በፈጸመው ጥፋት እርሱን አለመቅጣት ማለት ነው።
* ቃሉ “ዕዳ መሰረዙን” በሚያመለክት መልኩ፣ “መሰረዝ” የሚል ትርጕም ባለው መልኩ ምሳሌያዊ አነጋገርም ይሆናል።
* ሰዎች ኀጢአታቸውን ሲናዘዙ ከኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕታዊ ሞት የተነሣ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል።
* እርሱ ይቅር እንዳላቸው እነርሱም ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለባቸው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አስተማረ።

8
bible/kt/forsaken.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# መርሳት፣ ተረሳ
“መርሳት” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ጨርሶ መተው ማለት ነው። “የተረሳ” በሌላው ወገን ጨርሶ የተተወ ግምት ውስጥ የማይገባ ሰው ነው።
* ሰዎች እግዚአብሔርን “ረሱ” ከተባለ ለእርሱ ታማኝ አይደሉም፤ ለእርሱ አይታዘዙም ማለት ነው።
* እግዚአብሔር ሰዎችን “ረሳ” ከተባለ እርሱ አይረዳቸውም፤ እንደ ገና ወደ እርሱ እንዲመለሱ የተለያየ መከራና ችግር እንዲደርስባቸው ይተዋቸዋል ማለት ነው።
* መዘንጋት ወይም የእግዚአብሔርን ትምህርት አለመከተል ማለትም ነው።
* “መርሳት” የሚለው ቃል፣ “ረስታችኋል” ወይም “ተረስታችኋል” በሚል የኀላፊ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።

7
bible/kt/fulfill.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# መፈጸም
“መፈጸም” አንዳች የሚጠበቅ ነገርን ፈጽሞ ወይም አከናውኖ መገኘት ማለት ነው።
* ትንቢት ሲፈጸም፣ በትንቢቱ የተነገረውን እግዚአብሔር እንዲፈጸም አደረገ ይባላል።
* አንድ ሰው የገባውን ቃል ሲጠብቅ፣ ሰውየው አደርጋለሁ ያለውን ፈጽሟል ማለት ነው።
* ኀላፊነትን መወጣት የተሰጠውን ወይም የተጠየቀውን ተግባር መፈጸም ማለት ነው።

9
bible/kt/gentile.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# አሕዛብ
አሕዛብ የያዕቆብ ወይም የአሥራ ሁለቱ የእርሱ ልጆች ዘር ያልሆነ ሰው ነው። ስለሆነም አሕዛብ አይሁድ አይድለም ማለት ነው።
* ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አሕዛብ አልፎ አልፎ፣ “ያልተገረዙ” ተብለው ይጠራሉ፤ ምክንያቱም እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት አብዛኞቹ ወንዶች ልጆቻቸውን ስለማይገርዙ ነው።
* ያ እርሱ የተለየ ሕዝብ እንደሆኑ እግዚአብሔር አይሁድን በመምረጡ፣ አሕዛብ ባዕዳንና የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆን እንደማይችሉ አሰቡ።
* በታሪክ ውስጥ በተለያየ ጊዜ አይሁድም እስራኤላውያን ወይም ዕብራውያን ተብለው ተጠርተዋል። ሌሎች ግን አሕዛብ ተብለው የሚጠሩት።
* አሕዛብ የሚለውን፣ “አይሁድ ያልሆነ” ወይም፣ “እስራኤላዊ ያልሆነ” (ብሉይ ኪዳን) ብሎ መተርጎም ይቻላል።
* በባሕላቸው መሠረት አይሁድ ከአሕዛብ ጋር አይበሉም ነበር፤ ይህም በጥንት ቤተ ክርስቲያን ችግር ሆኖ ነበር።

8
bible/kt/gift.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ስጦታ
“ስጦታ” የሚለው ለሌላው ወገን የተሰጠ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ስጦታ የሚሰጠው በምላሹ ምንም ነገር ባለ መጠበቅ ነው።
* ለድኾች የሚሰጥ ገንዘብ፣ ምግብ፣ ልብስና ማንኛውም ነገር “ስጦታ” ይባላል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ወይም መሥዋዕትም፣ “ስጦታ” ይባላል።
* የድነት ስጦታ በኢየሱስ በማመን በኩል እግዚአብሔር የሰጥን ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ስጦታ” የሚለው ቃል ሌሎችን ለማገልገል እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ሁሉ ይሚሰጠውን የተለያዩ መንፈሳዊ ችሎታዎችን ያመለክታል።

8
bible/kt/glory.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ክብር፣ የከበረ
በአጠቃላይ “ክብር” ማለት ምስጋና፣ ውበትና የላቀ ታላቅነት ማለት ነው። ክብር ያለው ነገር “የከበረ” ይባላል።
* አንዳንዴ “ክብር” ታልቅ ዋጋ እና አስፈላጊነት ያለውን ነገር ያመለክታል። በሌላ ዐውድ ደግሞ ውበትን፣ ድምቀትን ወይም ፍርድን ያመለክታል።
* ለምሳሌ፣ “የእረኞች ክብር” የሚለው ሐረግ በጎቻቸው የሚግጡት ሳር በብዛት ያለበትን ለምለም የግጦሽ ቦታ ያመለክታል።
* በተለይ ደግሞ ክብር በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ካለ ማንኛውም ሰውና ማንኛውም ነገር እጅግ የበለጠ ክቡር የሆነው እግዚአብሔርን ያመለክታል። ባሕርዩ ሁሉ ክብሩንና ውበቱን ይገልጻል።
* “መክበር” ማለት በአንድ ነገር መጓደድ ወይም መመካትን ያመለክታል።

11
bible/kt/god.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,11 @@
# እግዚአብሔር
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው።
* እግዚአብሔር ሁሌም ነበረ፤ ምንም ነገር ከመሆኑ በፊት ነበረ፤ ለዘላለምም ይኖራል።
* አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ባለ ማንኛውም ነገር ሥልጣን ያለው እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው።
* እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅ፣ እጅግ ጠበኛ፣ ቅዱስ፥ ኀጢአት የሌለበት፣ መልካም መሐሪና አፍቃሪ ነው።
* እርሱ ኪዳን አክባሪ አምላክ ነው፤ እርሱ ተስፋ ቃሉን የሚፈጽም ነው።
* ሰዎች የተፈጠሩት እርሱን ለማምለክ ነው፤ ማምለክ ያለባቸው እርሱን ብቻ ነው።
* ስሙ፣ “ያህዌ” መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ይህም “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “ሁሌም የምኖር” ማለት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ሕላዌ ስለሌላቸውና ሰዎች በስሕተት ስለሚያመልኳቸው ስለ ሐሰተኛ አማልክትም ይናገራል።

6
bible/kt/godly.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# አምላካዊ፣ አምላካዊነት
“አምላካዊ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን በሚያስከብርና የእግዚአብሔርን ማንነት በሚያሳይ መንገድ የሚኖር ሰውን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማድረግ እርሱን የማያከብር ሰው ባሕርይ አምላካዊነት ይባላል።
* አምላካዊ ባሕርይ ያለው ሰው ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግሥትን፣ ቸርነትንና ራስን መግዛትን የመሳሰሉ የመንፈስ ፍሬ በሕይወቱ ይታያሉ።
* የአምላካዊነት ባሕርይ ማለትም፣ እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ መኖር፣ መንፈስ ቅዱስ ውስጡ ለመሆኑና ለእርሱም እየተገዛ መሆኑን የሚያሳይ ፍሬ ወይም ውጫዊ ማስረጃ ነው።

7
bible/kt/godthefather.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# እግዚአብሔር አብ፣ ሰማያዊ አባት፣ አባት
“እግዚአብሔር አብ” እና፣ “ሰማያዊ አባት” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት አንዱን እውነተኛ አምላክ ያህዌን ነው። ይህ ቃል በተለይም ኢየሱስ ሲጠቀምበት “አባት” ተብሎም ተጠርቷል።
* እግዚአብሔር - እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ተጠርቷል። እያንዳንዱ አካል ፍጹም አምላክ ነው፤ ይሁን እንጂ ያለው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችሉት ምስጢር ነው።
* እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር አልድን (ኢየሱስን) ወደ ዓለም ላከ እርሱም መንፈስ ቅዱስን ለሕዝቡ ላከ።
* በእግዚአብሔር ወልድ የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ይሆናል፤ መንፈስ ቅዱስ በዚያ ሰው ውስጥ ለመኖር ይመጣል። ይህ የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችለው ምስጢር ነው።

12
bible/kt/good.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,12 @@
# መልካም፣ መልካምነት
“መልካም” የሚለው ቃል እንደ ምንባቡ ዐውድ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። እነዚህን የተለያዩ ቃሎች ለመተርጎም የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጕሞች ያቀርባሉ።
* አጠቃላይ በሆነ መልኩ ከእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ዓላማና ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነገር መልካም ነው።
* “መልካም” ነገር ደስ የሚያሰኝ፣ የላቀ ብልጫ ያለው፣ ሰዎችን የሚረዳ፣ ምቹ፣ ጠቃሚ ወይም ከግብረ ገብ አንጻር ትክክል ሊሆን ይችላል።
* “መልካም” መሬት፣ “ለም” ወይም፣ “ፍሬያማ” ተብሎ ይጠራል።
* “መልካም” ሰብል፣ ብዛት ያለው ሰብል ይባላል።
* እንደ “መልካም ገበሬ” ሁሉ አንድ ሰው በሥራውና በሙያው ጠንቃቃና የተዋጣለት ከሆነ፣ “መልካም” ይባላል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ”መልካም” አጠቃላይ ትርጕም “ከክፉ” ጋር በንጽጽR ነው የሚቀርበው።
* “መልካምነት” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያማለክተው ግብረ ገባዊ ጥራትን ወይም በሐሳብና በተግባር ጻድቅ ሆኖ መገኘትን ነው።
* የእግዚአብሔር መልካምነት መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን ለሰዎች በመስጠት እነርሱን መባረኩን ያመለክታል። ግብረ ገባዊ ፍጽምናውንም ሊያመለክት ይችላል።

6
bible/kt/goodnews.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# የምሥራች፣ ወንጌል
ቃል በቃል የምሥራች ማለት ሲሆን፣ ሰዎችን የሚጠቅምና ደስ የሚያሰኛቸውን መልእክት ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው በኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕት መሆን አማካይነት እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን ድነት ነው።
* በአብዛኞቹ የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች “የምሥራች” የሚለው ቃል፣ “ወንጌል” ተብሎ ተተርጉሞአል። ለምስሌ፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል” እና፣ “የመንግሥቱ ወንጌል” ከተሰኙት ሐረጎች መመልከት ይቻላል።

7
bible/kt/grace.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ጸጋ፣ ባለጸጋ
“ጸጋ” የሚለው ቃል ምንም ሳይለፋና ሳይደክም አንድን ሰው መርዳትን ወይም መባረክን ያመለክታል። “ባለ ጸጋ” ሌሎችን ጸጋ የሚያሳይን ሰው ይመለከታል።
* እግዚአብሔር ለኀጢአተኛ የሰው ልጆች ያለው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ስጦታ ነው።
* ጸጋ በደልና የሚጎዳ ነገር የፈጸመውን ሰው ይቅር ማለትንና ለእርሱ ደግ መሆንንም ያመለክታል።
* “ጸጋ ማግኘት” ከእግዚአብሔር ረድኤትና ምሕረትን መቀበልን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አንድን ሰው አስመልክቶ እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶ እነርሱን መርዳቱን የሚያመለክት ትርጕምንም ይጨምራል።

6
bible/kt/guilt.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# የበደል መሥዋዕት
“በደል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኀጢአት ማድረግን ወይም ወንጀል መፈጸምን ነው።
* “መበደል” ግብረ ገባዊ ያልሆነ ነገር ማድረግ ማለትም በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ማለት ነው።
* “የበደል” ተቃራኒ፣ “ንጹሕነት” ነው።

7
bible/kt/hades.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ሐዴስ፣ ሲኦል
ሞትንና ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበትን ቦታ ለማመልከትት “ሐዴስ” እና “ሲኦል” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የሁለቱም ትርጕም ተመሳሳይ ነው።
* የሙታን ስፍራን በአጠቃላይ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ “ሲኦል” የተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ ነፍሳትን ቦታ ለማመልከት “ሐዴስ” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል። እነዚህ ነፍሳት ወደ ሐዴስ እንደሚወርዱ ተነግሯል። አንዳንዴ ይህ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሰማይ፣ “መውጣት” ጋር በንጽጽር ይቀመጣል።
* የዮሐንስ ራእይ ውስጥ፣ “ሐዴስ” የሚለው ቃል፣ “ሞት” ከተሰኘው ቃል ጋር በአንድነት ቀርቧል። መጨረሻው ዘመን ላይ ሞትና ሐዴስ ወደ እሳቱ ባሕር ይጣላሉ፤ እርሱም ገሃነም ነው።

8
bible/kt/heart.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ልብ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወም ፈቃድ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
* “ልበ ጠንካራ” መሆን ሰውየው በግትርነት ለእግዚአብሔር መታዘዝ አለመፈለጉን የሚያሳይ የተለመደ አገላለጽ ነው።
* “በፍጹም ልቤ” ወይም፣ “በሙሉ ልቤ” የተሰኙት አገላለጾች ምንም ወደ ኋላ ሳይባል፣ በሙሉ መሰጠትና ፈቃደኛነት አንድን ነገር ማድረግን ያመለክታሉ።
* “በልብህ ያዘው” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ለአንድ ሰው የተለየ ከበሬታ መስጠት ማለት ነው።
* “ልበ ሰባራ” የሚለው ሐረግ ከፍ ያለ ሐዘንን ያመለክታል። የሰውየው ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል ማለት ነው።

8
bible/kt/heaven.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ሰማይ፣ ሰማያት፣ ሰማያዊ
“ሰማይ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል የእግዚአብሔር መኖሪያን ያመለክታል።
* “ሰማያት” የሚለው ቃል ፀሐይ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ጨምሮ ከምድር በላይ የምንመለከተውን ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ምድር ላይ ሆነን በቀጥታ የማናያቸውን በሩቅ ያሉ ፕላኔቶችን ጨምሮ የሰማይ አካላትን ሁሉ ያጠቃልላል።
* “ሰማይ” ደመናና የምንተነፍሰው አየር ያለበትን ከምድር በላይ ያለውን የተንጣለለ ሰማያዊ ቦታ ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት፣ “በላይ በሰማይ” መሆናቸው ይነገራል።
* በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ዐውዶች መሠረት “ሰማይ” እንዲሁ ከምድር በላይ የተንጣለለው ሰማያዊ ቦታ ወይም የእግዚአብሔርን መኖሪያ ያመለክታል።
* “ሰማይ” በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመልከት ነው። ለምሳሌ ማቴዎስ ስለ “መንግሥተ ሰማይ” ሲናገር ስለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” መናገሩ ነው።

6
bible/kt/hebrew.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
# ዕብራዊ
“ዕብራውያን” በይስሐቅና በያዕቆብ ዘር ሐረግ በኩል የተገኙ የአብርሃም ዘሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ዕብራዊ” ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሰው አብርሃም ነበር። “ዕብራውያን” በይስሐቅና በያዕቆብ ዘር ሐረግ በኩል የአብርሃም ዘር የሆኑ ሕዝብ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዕብራው” ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሰው አብርሃም ነው።
* “ዕብራዊ” የሚለው ቃል ዕብራውያን የሚናገሩትንም ቋንቋ ያመለክታል። መጀመሪያ ላይ ብሉይ ኪዳን የተጻፈው በዕብራይስ ቋንቋ ነበር።
* ዕብራውያን፣ “የአይሁድ ሕዝብ” ወይም እስራኤላውያን ተብለውም ይጠራሉ። እነዚህ ቃሎች ስለ አንድ ሕዝብ የሚያመለክቱ እንደ መሆናቸው መጠን ሦስቱንም ቃሎች የመጀመሪያው ቅጂ ላይ በተጻፉበት ቅጂ መሠረት ማስቀመጡ ተገቢ ነው።

7
bible/kt/hell.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ገሃነም፣ የእሳት ባሕር
ገሃነም በእርሱ ላይ የሚያምፁትንና በኢየሱስ መሥዋዕትነት በኩል እነርሱን የማድኑን ዕቅድ ችላ የሚሉትን የሚቀጣበት የመጨረሻው የስቃይ ቦታ ነው። “የእሳት ባሕር” ተብሎም ይጠራል።
* ገሃነም የእሳትና የጽኑ ስቃይ ቦታ መሆኑ ተነግሯል።
* ሰይጣንና እርሱን የሚከተሉ ርኵሳን መናፍስት ለዘላለም ቅጣት ወደ ገሃነም ይጣላሉ።
* ኢየሱ ለኀጢአታቸው መሥዋዕት መሆኑን የማያምኑና እርሱ እንደሚያድናቸው የማይተማመኑ ሰዎች ለዘላለም በገሃነም ይቀጣሉ።

7
bible/kt/highpriest.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ሊቀ ካህን
“ሊቀ ካህን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተቀሩት እስራኤላውያን ካህናት መሪ በመሆን ለአንድ ዓመት እንዲያገለግል የተሾመ የተለየ ካህንን ያመለክታል።
* ሊቀ ካህን የተለየ ኀላፊነቶች ነበር። በዓመት አንድ ጊዜ የሆነውን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ የሚፈቀድለት እርሱ ብቻ ነበር።
* እስራኤላውያን ብዙ ካህናት ቢኖሯቸውም ለአንድ ዘመን አንድ ሊቀ ካህን ብቻ ነበራቸው።
* ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህን ቀያፋ ነበር። የቀያፋ ሚስት አባት የነበረው የቀድሞው ሊቀ ካህንና ምናልባትም ከዚያ በኋላም በሕዝቡ ላይ ኀይልና ሥልጣን የነበረው ሐና አልፎ ይጠቀሳል።

10
bible/kt/holy.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# ቅዱስ፣ ቅድስና
“ቅዱስ” እና “ቅድስና” ኀጥእ ከሆነውና ፍጽምና ከሌለው ማንኛውም ነገር ፍጹም ልዩ የሚያደርገውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያመለክታል።
* ፍጹም ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰዎችንም ሆነ ነገሮችን ቅዱስ ያደርጋል።
* ቅዱስ ሰው የእግዚአብሔር ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር ለማምጣት ዓላማ ተለይቷል።
* እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን የተናገረለት ነገር ማለት ለእርሱ መሥዋዕት እንዲቀርብበት መሠዊያ ለእርሱ ክብርና አገልግሎት ተለይቶአል።
* እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ካላቀረባቸው በቀር ሰዎች ወደ እርሱ መቅረብ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሰዎች ኀጢአተኞችና ፍጽምና የጎደላቸው ናቸው።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለእርሱ ልዩ አገልግሎት ካህናትን ቅዱስ አድርጎ ይለይ ነበር። ወደ እርሱ መቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ሥርዐት በመፈጸም ከኀጢአት ነጽተዋል።
* የእርሱ የሆኑትን ወይም ቤተ መቅደሱን የመሰሉ እርሱ ራሱን የገለጠበትን ቤተ መቅደሱን እንደመዳሰሉት አንዳንድ ቦታዎችንና ነገሮችን እግዚአብሔር ቅዱስ አድርጎ ለይቶአል።

7
bible/kt/holyone.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
# ቅዱስ
“ቅዱሱ” የሚለው መጠሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሌም የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ መጠሪያ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው፣ “የእስራኤል ቅዱስ” በተሰኘው ሐረግ ውስጥ ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስም፣ “ቅዱሱ” ተብሎ ተጠርቷል።
* “ቅዱሱ” የሚለው ቃል አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልአክን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።

10
bible/kt/holyplace.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,10 @@
# ቅድስት፣ ቅድስተ ቅዱሳን
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቅድስት” እና፣ “ቅድስተ ቅዱሳን” የተሰኙ ቃሎች መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ክፍሎች ያመለክታሉ። አንዳንዴ፣ “ቅድስት” ወይም፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው በጠቅላላው ለእግዚአብሔር የለለየ ማንኛውንም ቦታ ያመለክታል።
* ቅድስት” እና “ቅድስተ ቅዱሳን” በአጥር በተከለለ መገናኛ ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ አደባባይ የተከበበ ቦታ ነበር የሚገኙት። ቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ላይ በጣም ወፍራምና ከባድ መጋረጃ ነበር።
* እስራኤላውያንን ሁሉ ከሚወክለው ከላቀ ካህኑ ጋር ለመገናኘት እግዚአብሔር ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይመጣ ነበር።
* ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ እንዲገባ የሚፈቀደው ለሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር። ወፍራምና ከባድ መጋረጃ ማንም ወደዚያ እንዳይገባ ያግዳል።
* “ቅድስት” ወይም፣ “ቅድስት ቦታ” የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ውስጡ ሁለት ነገሮች ነበሩ፤ የዕጣን መሠዊያና የተቀደሰው እንጀራ ያለበት መንበር።
* “ቅድስተ ቅዱሳን” ሁለተኛው ክፍል ሲሆን በጣም ወደ ውስጥ ሲገባ የሚገኘው ነው፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚህ ውስጥ ነበር።
* አንዳንዴ፣ “ቅድስት” ወይም፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው በአጠቃላይ የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ወይም መገናኛ ድንኳኑን ያመለክታል።

9
bible/kt/holyspirit.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,9 @@
# መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ
እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት።
* መንፈስ ቅዱስ አንዳንዴ፣ “መንፈስ” እና “የያህዌ መንፈስ” እና፣ “የእውነት መንፈስ” ተብሏል።
* መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ፍጹም ቅዱስ፣ እጅግ ንጹሕ፣ በባሕርዩና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍጹም ጻድቅ ነው።
* ከአብና ከወልድ ጋር መንፈስ ቅዱስ ዓለምን በመፍጠር ተሳታፊ ነበር።
* እግዚአብሔር ወልድ ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ ሕዝቡን እንዲመራቸው፣ እንዲያስተምራቸው፣ እንዲያጽናናቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲያስችላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ላከ።
* መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን መራው፤ በኢየሱስ የሚያምኑትንም ይመራቸዋል።

8
bible/kt/honor.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
# ክብር፣ ማክበር
“ክብር” የሚለው ቃል ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው ልጅ የሚሰጥ የላቀ ቦታ፣ ግምት ወይም አክብሮታዊ ፍርሃት ነው።
* ሌሎችን እንዲያከብሩ ለራሳቸው ግን ክብር መፈለግ እንደሌለባቸው እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ተናግሮአል።
* ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ተነግሮአቸዋል፤ ይህም መታዘዝንም ይጨምራል።
* በተለይ ስለ ኢየሱስ በሚነገርበት ጊዜ፣ “ክብርና ግርማ” በአንድነት ተያይዘው ይቀርባሉ። አንድን ነገር የሚያመለክቱ ሁለት የተለያዩ የአገላለጽ መንገዶችን የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ።
* እግዚአብሔርን ማክበር ለእርሱ መታዘዝንና የእርሱን ታላቅነት በሚያሳይ መንገድ መኖርንም ያጠቃልላል፥

Some files were not shown because too many files have changed in this diff Show More