am_tw/bible/names/peter.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ጴጥሮስ፣ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ኬፋ
እነዚህ ስሞች ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ የነበረው የጴጥሮስ መጠሪያዎች ናቸው። በጥንት ቤተ ክርስቲያን ታዋቂ መሪ ነበር።
* ኢየሱስ እርሱን ከመጥራቱ በፊት ይህ ሰው ስምዖን ይባል ነበር።
* በኋላ ላይ ኢየሱስ፣ ኬፋ በማለትም ጠርቶታል፤ ይህም በአረማይክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው። ጴጥሮስ ተብሎም ተጠርቷል፤ ይህም በግሪክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው።
* በጣም የሚታወቀው ጴጥሮስ ወይም ስምዖን ጴጥሮስ በተሰኘው ስሙ ነው።
* ሰዎችን ለመፈወሰና የኢየሱስን የምሥራች ቃል ለመስበክ እግዚአብሔር በጴጥሮስ ተጠቅሟል።
* አማኝ ወገኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር ጴጥሮስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ሁለት መልእክቶች ጽፏል።