# ጴጥሮስ፣ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ኬፋ እነዚህ ስሞች ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ የነበረው የጴጥሮስ መጠሪያዎች ናቸው። በጥንት ቤተ ክርስቲያን ታዋቂ መሪ ነበር። * ኢየሱስ እርሱን ከመጥራቱ በፊት ይህ ሰው ስምዖን ይባል ነበር። * በኋላ ላይ ኢየሱስ፣ ኬፋ በማለትም ጠርቶታል፤ ይህም በአረማይክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው። ጴጥሮስ ተብሎም ተጠርቷል፤ ይህም በግሪክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው። * በጣም የሚታወቀው ጴጥሮስ ወይም ስምዖን ጴጥሮስ በተሰኘው ስሙ ነው። * ሰዎችን ለመፈወሰና የኢየሱስን የምሥራች ቃል ለመስበክ እግዚአብሔር በጴጥሮስ ተጠቅሟል። * አማኝ ወገኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር ጴጥሮስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ሁለት መልእክቶች ጽፏል።