am_tn/isa/28/27.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለኢየሩሳሌም ምሳሌ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች ተመልከት)

ጥቁር አዝሙድ በተሳለች ማሄጃ አያኬድም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬው የጥቁር አዝሙድን ፍሬ ከተክሉ በከባድ ማሄጃ አይለይም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ጥቁር አዝሙድ

ይህንን በኢሳይያስ 28፡25 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ወይም የሰረገላ መንኮራኩር በከሙን ላይ አያዞርም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ወይም ከባድ መንኮራኩር በከሙን ዘር ላይ አያሽከረከርም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ከሙን

ይህንን በኢሳይያስ 28፡25 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ነገር ግን ጥቁር አዝሙድ በሽመል ከሙኑንም በበትር ይወቃል

ፍሬውን ከተክሉ ለመለየት ለገበሬው ትክክለኛ የሆነውን መንገድ ኢሳይያስ ይገልጻል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ነገር ግን ጥቁር አዝሙዱን በሽመል ይወቃዋል፣ ከሙንም በዱላ ይወቃዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

እህል ለእንጀራ ይወቃል እንጂ ፈጽሞ አይደቅም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬ እህልን ለእንጀራ ይወቃዋል እንጂ በጣም ትንንሽ እንዲሆን አይወቃውም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)