# አጠቃላይ መረጃ ኢሳይያስ ለኢየሩሳሌም ምሳሌ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች ተመልከት) # ጥቁር አዝሙድ በተሳለች ማሄጃ አያኬድም ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬው የጥቁር አዝሙድን ፍሬ ከተክሉ በከባድ ማሄጃ አይለይም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት) # ጥቁር አዝሙድ ይህንን በኢሳይያስ 28፡25 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ # ወይም የሰረገላ መንኮራኩር በከሙን ላይ አያዞርም ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ወይም ከባድ መንኮራኩር በከሙን ዘር ላይ አያሽከረከርም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት) # ከሙን ይህንን በኢሳይያስ 28፡25 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ # ነገር ግን ጥቁር አዝሙድ በሽመል ከሙኑንም በበትር ይወቃል ፍሬውን ከተክሉ ለመለየት ለገበሬው ትክክለኛ የሆነውን መንገድ ኢሳይያስ ይገልጻል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ነገር ግን ጥቁር አዝሙዱን በሽመል ይወቃዋል፣ ከሙንም በዱላ ይወቃዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት) # እህል ለእንጀራ ይወቃል እንጂ ፈጽሞ አይደቅም ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬ እህልን ለእንጀራ ይወቃዋል እንጂ በጣም ትንንሽ እንዲሆን አይወቃውም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)