am_tn/rom/14/01.md

20 lines
986 B
Markdown

# አያያዥ ሀሳብ
ጳውሎስ አማኞች በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ አንደሆኑ እንዲያስታውሱ ያበረታታቸዋል።
# በእምነት ደካማ
ይህ የሚወክለው አንዳንድ ነገሮችን በመብላታቸው የወቀሳ ስሜት የሚሰማቸውን ሰዎች ነው።
# በክርክራቸው ሳትፈርዱባቸው
“እናም በአስተሳሰባቸው ምክንያት አትክሰሷቸው”
# አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት እምነት አለው
እዚህ ላይ “እምነት” የሚለው ቃል አንድ ሰው እግዚአብሔር አድርግ ብሎኛል ብሎ የሚያምነውን ነገር ማድረግን ያመለክታል።
# ሌላው ደካማ የሆነው ደግሞ አትክልትን ብቻ ይበላል
ይህ እርሱ ስጋን እንዲበላ እግዚአብሔር እንደማይፈልግ የሚያምንን ሰው ይገልጻል።