am_tn/rom/14/01.md

986 B

አያያዥ ሀሳብ

ጳውሎስ አማኞች በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ አንደሆኑ እንዲያስታውሱ ያበረታታቸዋል።

በእምነት ደካማ

ይህ የሚወክለው አንዳንድ ነገሮችን በመብላታቸው የወቀሳ ስሜት የሚሰማቸውን ሰዎች ነው።

በክርክራቸው ሳትፈርዱባቸው

“እናም በአስተሳሰባቸው ምክንያት አትክሰሷቸው”

አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት እምነት አለው

እዚህ ላይ “እምነት” የሚለው ቃል አንድ ሰው እግዚአብሔር አድርግ ብሎኛል ብሎ የሚያምነውን ነገር ማድረግን ያመለክታል።

ሌላው ደካማ የሆነው ደግሞ አትክልትን ብቻ ይበላል

ይህ እርሱ ስጋን እንዲበላ እግዚአብሔር እንደማይፈልግ የሚያምንን ሰው ይገልጻል።