# አያያዥ ሀሳብ ጳውሎስ አማኞች በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ አንደሆኑ እንዲያስታውሱ ያበረታታቸዋል። # በእምነት ደካማ ይህ የሚወክለው አንዳንድ ነገሮችን በመብላታቸው የወቀሳ ስሜት የሚሰማቸውን ሰዎች ነው። # በክርክራቸው ሳትፈርዱባቸው “እናም በአስተሳሰባቸው ምክንያት አትክሰሷቸው” # አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት እምነት አለው እዚህ ላይ “እምነት” የሚለው ቃል አንድ ሰው እግዚአብሔር አድርግ ብሎኛል ብሎ የሚያምነውን ነገር ማድረግን ያመለክታል። # ሌላው ደካማ የሆነው ደግሞ አትክልትን ብቻ ይበላል ይህ እርሱ ስጋን እንዲበላ እግዚአብሔር እንደማይፈልግ የሚያምንን ሰው ይገልጻል።