am_tn/rom/10/01.md

24 lines
1.2 KiB
Markdown

# አያያዥ ዐረፍተ ነገር፥
ጳውሎስ እስራኤል በክርስቶስ እንዲያምን ምኞቱን እየገለጸ ግን ደግሞ አይሁድም ሆነ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉም ሊድኑ የሚችሉት በኢየሱስ ባላቸው እምነት ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያስገነዝባል።
# ወንድሞች
እዚህ ላይ እንዲህ ማለት ወንዶችንም ሴቶችንም ጨምሮ ክርስቲያን ወገኞች ለማለት ነው።
# የልቤ ምኞት
እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሰውን ውስጣዊ ስሜት ለማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “ከሁሉም የሚበልጥ ፍላጎቴ”
# ለእነርሱ ነው፤ ለድነታቸው
“እግዚአብሔር አይሁዶችን ያድናቸዋል”
# እኔ ስለ እነርሱ እመሰክራለሁ
“እኔ ስለ እነርሱ እውነቱን እናገራለሁ”
# እነርሱ የእግዚአብሔርን መመዘኛ ሐሳብ አላወቁም
እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር መመዘኛ ሐሳብ” የሚለው እግዚአብሔር ሰዎችን በፊቱ ሐሳቡን የሚያሟሉ የሚያደርግበት መንገድን ያመለክታል።