# አያያዥ ዐረፍተ ነገር፥ ጳውሎስ እስራኤል በክርስቶስ እንዲያምን ምኞቱን እየገለጸ ግን ደግሞ አይሁድም ሆነ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉም ሊድኑ የሚችሉት በኢየሱስ ባላቸው እምነት ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያስገነዝባል። # ወንድሞች እዚህ ላይ እንዲህ ማለት ወንዶችንም ሴቶችንም ጨምሮ ክርስቲያን ወገኞች ለማለት ነው። # የልቤ ምኞት እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሰውን ውስጣዊ ስሜት ለማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “ከሁሉም የሚበልጥ ፍላጎቴ” # ለእነርሱ ነው፤ ለድነታቸው “እግዚአብሔር አይሁዶችን ያድናቸዋል” # እኔ ስለ እነርሱ እመሰክራለሁ “እኔ ስለ እነርሱ እውነቱን እናገራለሁ” # እነርሱ የእግዚአብሔርን መመዘኛ ሐሳብ አላወቁም እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር መመዘኛ ሐሳብ” የሚለው እግዚአብሔር ሰዎችን በፊቱ ሐሳቡን የሚያሟሉ የሚያደርግበት መንገድን ያመለክታል።