am_tn/rom/10/01.md

1.2 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር፥

ጳውሎስ እስራኤል በክርስቶስ እንዲያምን ምኞቱን እየገለጸ ግን ደግሞ አይሁድም ሆነ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉም ሊድኑ የሚችሉት በኢየሱስ ባላቸው እምነት ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያስገነዝባል።

ወንድሞች

እዚህ ላይ እንዲህ ማለት ወንዶችንም ሴቶችንም ጨምሮ ክርስቲያን ወገኞች ለማለት ነው።

የልቤ ምኞት

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሰውን ውስጣዊ ስሜት ለማለት ነው። በሌላ አባባል፣ “ከሁሉም የሚበልጥ ፍላጎቴ”

ለእነርሱ ነው፤ ለድነታቸው

“እግዚአብሔር አይሁዶችን ያድናቸዋል”

እኔ ስለ እነርሱ እመሰክራለሁ

“እኔ ስለ እነርሱ እውነቱን እናገራለሁ”

እነርሱ የእግዚአብሔርን መመዘኛ ሐሳብ አላወቁም

እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር መመዘኛ ሐሳብ” የሚለው እግዚአብሔር ሰዎችን በፊቱ ሐሳቡን የሚያሟሉ የሚያደርግበት መንገድን ያመለክታል።