am_tn/psa/032/003.md

32 lines
1.9 KiB
Markdown

# ዐጥንቶቼ ተበላሹ
‹‹ዐጥንቶቼ›› የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየተጐዳሁ ነው›› ወይም፣ ‹‹የበለጠ እየደከምሁ ነው››
# ቀኑን ሙሉ
ይህም ማለት ‹‹ዘወትር›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ››
# ቀንና ሌሊት
እነዚህ ሁለት ጽንፎች በመካከል ያለውን ሁሉ ይጨምራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ››
# እጅህ ከብዳኛለችና
እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ይህ ሐረግ በሙሉ፣ ‹‹ጐዳኸኝ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም አሰቃየኸኝ››
# ኀይሌም የበጋ ድርቅ እንዳገኘው ተሟጠጠ
የዳዊት ኀይል በድርቅ ጊዜ እንደሚጠወልግ ትንሽ ለምለም ተክል ጋር ተመሳስሎአል፡፡
# ሴላ
ይህ እዚህ ላይ እንዴት እንደሚዘምሩ ወይም የሙዚቃ መሣሪያ እንደሚጫወቱ የሚያመለክት ሙዚቃዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ትርጒሞች የዕብራይስጡን ቃል ይጽፋሉ ሌሎች ትርጒሞች ግን ትተውታል፡፡ መዝሙር 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡
# በታላቅ ጭንቅ ጊዜ
‹‹በጣም በተጨነቁ ጊዜ››
# ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እነርሱ አጠገብ አይደርስም
አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ ጐርፍ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ችግሮች እንደ ጐርፍ ሲመጡ እነዚህ ሰዎች ምንም አይሆኑም››