# ዐጥንቶቼ ተበላሹ ‹‹ዐጥንቶቼ›› የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየተጐዳሁ ነው›› ወይም፣ ‹‹የበለጠ እየደከምሁ ነው›› # ቀኑን ሙሉ ይህም ማለት ‹‹ዘወትር›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ›› # ቀንና ሌሊት እነዚህ ሁለት ጽንፎች በመካከል ያለውን ሁሉ ይጨምራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ›› # እጅህ ከብዳኛለችና እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ይህ ሐረግ በሙሉ፣ ‹‹ጐዳኸኝ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም አሰቃየኸኝ›› # ኀይሌም የበጋ ድርቅ እንዳገኘው ተሟጠጠ የዳዊት ኀይል በድርቅ ጊዜ እንደሚጠወልግ ትንሽ ለምለም ተክል ጋር ተመሳስሎአል፡፡ # ሴላ ይህ እዚህ ላይ እንዴት እንደሚዘምሩ ወይም የሙዚቃ መሣሪያ እንደሚጫወቱ የሚያመለክት ሙዚቃዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ትርጒሞች የዕብራይስጡን ቃል ይጽፋሉ ሌሎች ትርጒሞች ግን ትተውታል፡፡ መዝሙር 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ # በታላቅ ጭንቅ ጊዜ ‹‹በጣም በተጨነቁ ጊዜ›› # ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እነርሱ አጠገብ አይደርስም አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ ጐርፍ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ችግሮች እንደ ጐርፍ ሲመጡ እነዚህ ሰዎች ምንም አይሆኑም››