am_tn/psa/032/003.md

1.9 KiB

ዐጥንቶቼ ተበላሹ

‹‹ዐጥንቶቼ›› የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየተጐዳሁ ነው›› ወይም፣ ‹‹የበለጠ እየደከምሁ ነው››

ቀኑን ሙሉ

ይህም ማለት ‹‹ዘወትር›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ››

ቀንና ሌሊት

እነዚህ ሁለት ጽንፎች በመካከል ያለውን ሁሉ ይጨምራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁልጊዜ››

እጅህ ከብዳኛለችና

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ይህ ሐረግ በሙሉ፣ ‹‹ጐዳኸኝ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም አሰቃየኸኝ››

ኀይሌም የበጋ ድርቅ እንዳገኘው ተሟጠጠ

የዳዊት ኀይል በድርቅ ጊዜ እንደሚጠወልግ ትንሽ ለምለም ተክል ጋር ተመሳስሎአል፡፡

ሴላ

ይህ እዚህ ላይ እንዴት እንደሚዘምሩ ወይም የሙዚቃ መሣሪያ እንደሚጫወቱ የሚያመለክት ሙዚቃዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ትርጒሞች የዕብራይስጡን ቃል ይጽፋሉ ሌሎች ትርጒሞች ግን ትተውታል፡፡ መዝሙር 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

በታላቅ ጭንቅ ጊዜ

‹‹በጣም በተጨነቁ ጊዜ››

ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እነርሱ አጠገብ አይደርስም

አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ ጐርፍ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ችግሮች እንደ ጐርፍ ሲመጡ እነዚህ ሰዎች ምንም አይሆኑም››