am_tn/oba/01/17.md

45 lines
2.3 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ከቁጥር 16-21 እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ የኤዶምን ምድር እንደሚወርሱ በእብዲዩ በኩል ይናገራል፡፡
# የሚያመልጡ ይሆናሉ
እነዚህ እግዚአብሔር ከተማዋን ቀጥቶ ካበቃ በኋላ በሕይወት ያሉ የእሩሳሌም ህዝብ ናቸው ይህም በግልጽ ተርጓሚው “ከእግዚአብሔር ቅጣት ያመለጡ የተወሰኑ የእስራኤል ህዝቦች” ማለት ነው፡፡
# እርሱም ቅዱስ ይሆናል
“እርሱ”የሚለው ቃል የፅዮን ተራራን ያመለክታል፡፡
# የያዕቆብን ቤት እሳት የዮሴፍን ቤት ነበልባልም
እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብና ዮሴፍ ቤት ሲናገር እሳት እንዲሆኑ አድርጎ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክኒያት ኤሳውን ልክ እንደ እሳት ፈጥነው ጨርሰው ስለሚያጠፉ ነው፡፤
# የያዕቆብ ቤት
ቤት የሚለው ቃል ዘይቤያዊ ሲሆን በቤት ውስጥ ስለሚኖረው ነፍስ( ህይወት) ለማለት ነው፡፡ በዙህ መልኩ የይዕቆብን የዘር ሐረግ( ነገድ) ለማመልከት ነው፡፡
ተርጓሚው - ዬዕቆብ የዘር ሐረግ ( ነገድ)
# ገለባ
እህል ከተወቃበት ( ከተሰበሰበ) በኋላ መሬት ላይ የሚቀር
# እነርሱንም
ይህ ቃል የሚያመለክተው የያዕቆብና የዮሴፍ ቤትን ነው፡፡
# ያቃጥሏቸዋል
ያቃጥሏቸዋል የሚለው የኤዶም ሕዝብ የሆኑትን ኤሳውን የዘር ሐረግ ይወክላል፡፡
# ከኤሳው ቤት ቅሬታ የለውም
“አንድም ሰው ከለኤሳው ቤት አይተርፍም”
# የኤሳው ቤት
ቤት የሚለው ቃል ዘይቤያዊ ሲሆን በቤት ውስጥ ስላሉት የቤተሰብ አባላት ነው፡፡ ይህም የኤሳው የዘር ሐረግ ይወክላል፡፡ ተርጓሚው “የኤሳው የዘር ሃረግ” ( ዘይቤን ተመልከት)
# እግዚአብሄርም ተናግሯልና
ይህ የቃለ መሃላ ቀመር ሲሆን እግዚአብሄር ስለተናገረ ብቻ የሚፈፅም መሆኑን ነው፡፤