# አጠቃላይ መረጃ ከቁጥር 16-21 እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ የኤዶምን ምድር እንደሚወርሱ በእብዲዩ በኩል ይናገራል፡፡ # የሚያመልጡ ይሆናሉ እነዚህ እግዚአብሔር ከተማዋን ቀጥቶ ካበቃ በኋላ በሕይወት ያሉ የእሩሳሌም ህዝብ ናቸው ይህም በግልጽ ተርጓሚው “ከእግዚአብሔር ቅጣት ያመለጡ የተወሰኑ የእስራኤል ህዝቦች” ማለት ነው፡፡ # እርሱም ቅዱስ ይሆናል “እርሱ”የሚለው ቃል የፅዮን ተራራን ያመለክታል፡፡ # የያዕቆብን ቤት እሳት የዮሴፍን ቤት ነበልባልም እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብና ዮሴፍ ቤት ሲናገር እሳት እንዲሆኑ አድርጎ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክኒያት ኤሳውን ልክ እንደ እሳት ፈጥነው ጨርሰው ስለሚያጠፉ ነው፡፤ # የያዕቆብ ቤት ቤት የሚለው ቃል ዘይቤያዊ ሲሆን በቤት ውስጥ ስለሚኖረው ነፍስ( ህይወት) ለማለት ነው፡፡ በዙህ መልኩ የይዕቆብን የዘር ሐረግ( ነገድ) ለማመልከት ነው፡፡ ተርጓሚው - ዬዕቆብ የዘር ሐረግ ( ነገድ) # ገለባ እህል ከተወቃበት ( ከተሰበሰበ) በኋላ መሬት ላይ የሚቀር # እነርሱንም ይህ ቃል የሚያመለክተው የያዕቆብና የዮሴፍ ቤትን ነው፡፡ # ያቃጥሏቸዋል ያቃጥሏቸዋል የሚለው የኤዶም ሕዝብ የሆኑትን ኤሳውን የዘር ሐረግ ይወክላል፡፡ # ከኤሳው ቤት ቅሬታ የለውም “አንድም ሰው ከለኤሳው ቤት አይተርፍም” # የኤሳው ቤት ቤት የሚለው ቃል ዘይቤያዊ ሲሆን በቤት ውስጥ ስላሉት የቤተሰብ አባላት ነው፡፡ ይህም የኤሳው የዘር ሐረግ ይወክላል፡፡ ተርጓሚው “የኤሳው የዘር ሃረግ” ( ዘይቤን ተመልከት) # እግዚአብሄርም ተናግሯልና ይህ የቃለ መሃላ ቀመር ሲሆን እግዚአብሄር ስለተናገረ ብቻ የሚፈፅም መሆኑን ነው፡፤