am_tn/jer/46/01.md

1.9 KiB

አጠቃላይ ሀሳብ

ኤርምያስ በብዛት ትንቢትን በግጥም መልክ ይፅፋል፡፡ የእብረዊያን ፀሀፊዎች የተለያዩ ንፅፅር ይጠቀሙ ነበር፡፡

ወደ ነብዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሄር ቃል ይህ ነው፡፡

ይህ ልዩ የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ኤርምያስ 14፡1 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት፡፡ “ይህ የእግዚአብሄር ቃል ለኤርምያስ የተሰጠ ነው”

ስለ ግብፅ

ይህ ሀረግ የግብፅ ከተማን ያመለክታል

ኒካዑ

ይህ የወንድ ስም ነው

ከርከሚሽ

ይህ በኤፍራጥስ በስተምእራብ በኩል የሚገኝ ከተማ ነው፡፡

የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር

ናቡከደነፆር የሚለው ሰራዊቱን ያመለክታል፡፡ “የባቢሎን የንጉስ ናቡከደነፆር ሰራዊት”

በኢዮአቄም በአራተኛው አመት

ይህ ከኢዮአቄም አራተኛ አመት ንግስና ነው፡፡ “ኢዮአቄም ከነገሰ በአራተኛው አመት ”

አራተኛው አመት

አራተኛው የሚለው አራት ቁጥርን ያመለክታል፡፡

ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ

ልጉዋም ማለት ፈረሶች ላይ የመታሰር ሲሆን ይህም ሰረገላውን ለመጎተት ይጠቅማል፡፡ “ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ” ሲል ሰራዊቶቹ ሰረገላው ሆነው ፈረሶቹ ሰረገላውን ይጎትቱታል፡፡

ራስ ቁርንም

በጦርነት ጊዜ የራስ ክፍልን ከአደጋ ለመከላከል የሚጠቅም ነው፡፡

ጦርንም ሰንግሉ

ይህ ሀረግ ጦሮቻችሁን ሳሉ ማለት ነው፡፡