am_tn/jer/46/01.md

44 lines
1.9 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ ሀሳብ
ኤርምያስ በብዛት ትንቢትን በግጥም መልክ ይፅፋል፡፡ የእብረዊያን ፀሀፊዎች የተለያዩ ንፅፅር ይጠቀሙ ነበር፡፡
# ወደ ነብዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሄር ቃል ይህ ነው፡፡
ይህ ልዩ የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ኤርምያስ 14፡1 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት፡፡ “ይህ የእግዚአብሄር ቃል ለኤርምያስ የተሰጠ ነው”
# ስለ ግብፅ
ይህ ሀረግ የግብፅ ከተማን ያመለክታል
# ኒካዑ
ይህ የወንድ ስም ነው
# ከርከሚሽ
ይህ በኤፍራጥስ በስተምእራብ በኩል የሚገኝ ከተማ ነው፡፡
# የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር
ናቡከደነፆር የሚለው ሰራዊቱን ያመለክታል፡፡ “የባቢሎን የንጉስ ናቡከደነፆር ሰራዊት”
# በኢዮአቄም በአራተኛው አመት
ይህ ከኢዮአቄም አራተኛ አመት ንግስና ነው፡፡ “ኢዮአቄም ከነገሰ በአራተኛው አመት ”
# አራተኛው አመት
አራተኛው የሚለው አራት ቁጥርን ያመለክታል፡፡
# ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ
ልጉዋም ማለት ፈረሶች ላይ የመታሰር ሲሆን ይህም ሰረገላውን ለመጎተት ይጠቅማል፡፡ “ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ” ሲል ሰራዊቶቹ ሰረገላው ሆነው ፈረሶቹ ሰረገላውን ይጎትቱታል፡፡
# ራስ ቁርንም
በጦርነት ጊዜ የራስ ክፍልን ከአደጋ ለመከላከል የሚጠቅም ነው፡፡
# ጦርንም ሰንግሉ
ይህ ሀረግ ጦሮቻችሁን ሳሉ ማለት ነው፡፡