am_tn/isa/59/09.md

16 lines
1.2 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡
# ፍትሕ ከእኛ ርቆአል
እዚህ ላይ፣ ‹‹እኛ›› የሚወክለው ኢሳይያስንና የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹ርቆአል›› ፍትሕ መጥፋቱንና ለማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፍትሕ ጠፍቷል፤ ለማግኘትም ያስቸግራል››
# ብርሃንን ጠበቅን ግን፣ ጨለማ አየን፤ የብርሃን ጸዳል ጠበቅን ግን በጨለማ እንሄዳለን፡፡
እያንዳንዱ ሐረግ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን መልካምነት ጠብቀው እንደ ነበርና እርሱ ግን የተዋቸው እንደሚመስል ያመለክታል፡፡
# እንደ ዕውር ቅጥሩ ላይ ተደናበርን… እንደ ሙታን
ይህ ማለት እግዚአብሔር ወደ እነርሱ ስለማይመጣ ትክክለኛውን መንገድ ለማግኘት ዐቅም እንደሌላቸው በወደ ፊቱም ተስፋ መቁረጣቸውንና በሕይወት ለመኖር ተስፋ እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡