# አጠቃላይ መረጃ ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡ # ፍትሕ ከእኛ ርቆአል እዚህ ላይ፣ ‹‹እኛ›› የሚወክለው ኢሳይያስንና የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹ርቆአል›› ፍትሕ መጥፋቱንና ለማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፍትሕ ጠፍቷል፤ ለማግኘትም ያስቸግራል›› # ብርሃንን ጠበቅን ግን፣ ጨለማ አየን፤ የብርሃን ጸዳል ጠበቅን ግን በጨለማ እንሄዳለን፡፡ እያንዳንዱ ሐረግ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን መልካምነት ጠብቀው እንደ ነበርና እርሱ ግን የተዋቸው እንደሚመስል ያመለክታል፡፡ # እንደ ዕውር ቅጥሩ ላይ ተደናበርን… እንደ ሙታን ይህ ማለት እግዚአብሔር ወደ እነርሱ ስለማይመጣ ትክክለኛውን መንገድ ለማግኘት ዐቅም እንደሌላቸው በወደ ፊቱም ተስፋ መቁረጣቸውንና በሕይወት ለመኖር ተስፋ እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡