am_tn/isa/59/09.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ፍትሕ ከእኛ ርቆአል

እዚህ ላይ፣ ‹‹እኛ›› የሚወክለው ኢሳይያስንና የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹ርቆአል›› ፍትሕ መጥፋቱንና ለማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፍትሕ ጠፍቷል፤ ለማግኘትም ያስቸግራል››

ብርሃንን ጠበቅን ግን፣ ጨለማ አየን፤ የብርሃን ጸዳል ጠበቅን ግን በጨለማ እንሄዳለን፡፡

እያንዳንዱ ሐረግ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን መልካምነት ጠብቀው እንደ ነበርና እርሱ ግን የተዋቸው እንደሚመስል ያመለክታል፡፡

እንደ ዕውር ቅጥሩ ላይ ተደናበርን… እንደ ሙታን

ይህ ማለት እግዚአብሔር ወደ እነርሱ ስለማይመጣ ትክክለኛውን መንገድ ለማግኘት ዐቅም እንደሌላቸው በወደ ፊቱም ተስፋ መቁረጣቸውንና በሕይወት ለመኖር ተስፋ እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡