am_tn/isa/07/01.md

1.8 KiB

በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን

‹‹አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ዘመን›› — ይህ ታሪኩ የተፈጸመበት ነው፡፡

ረአሶን… ፋቁሔ… ሮሜልዩ

የሰዎች ስም

ረአሶንና… ፋቁሔ… ወጡ

ነገሥታቱ የሚመሩት ሰራዊት እንደሆኑ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ረአሶንና… ፋቁሔ ከሰራዊታቸው ጋር ወጡ››

ሊወጉ ወጡ

ጸሐፊው፣ ከተማው ራሱ ውስጡ የሚኖሩ ሰዎች እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ››

ለዳዊት ቤት ወሬ በደረሰ ጊዜ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዳዊት ቤት ወሬውን ሰሙ››

የዳዊት ቤት

‹‹ቤት›› የሚለው ቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ቤተ ሰብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጉሥ አካዝና አማካሪዎቹ››

ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል

‹‹ሶርያ›› እና፣ ‹‹ኤፍሬም›› ነገሥታቶቻቸውን ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ኤፍሬም›› መላው ሰሜናዊ የእስራኤልን መንግሥት ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔን እየረዳ ነበር››

የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የእርሱና የሕዝቡ ልብ ተናወጠ

በዚህ ወሬ ልባቸው መናወጡ ነፋስ ሲያናውጠው ከሚናወጥ ዛፍ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አካዝና ሕዝቡ በጣም ፈሩ››