am_tn/isa/07/01.md

32 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን
‹‹አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ዘመን›› — ይህ ታሪኩ የተፈጸመበት ነው፡፡
# ረአሶን… ፋቁሔ… ሮሜልዩ
የሰዎች ስም
# ረአሶንና… ፋቁሔ… ወጡ
ነገሥታቱ የሚመሩት ሰራዊት እንደሆኑ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ረአሶንና… ፋቁሔ ከሰራዊታቸው ጋር ወጡ››
# ሊወጉ ወጡ
ጸሐፊው፣ ከተማው ራሱ ውስጡ የሚኖሩ ሰዎች እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ››
# ለዳዊት ቤት ወሬ በደረሰ ጊዜ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዳዊት ቤት ወሬውን ሰሙ››
# የዳዊት ቤት
‹‹ቤት›› የሚለው ቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ቤተ ሰብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጉሥ አካዝና አማካሪዎቹ››
# ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል
‹‹ሶርያ›› እና፣ ‹‹ኤፍሬም›› ነገሥታቶቻቸውን ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ኤፍሬም›› መላው ሰሜናዊ የእስራኤልን መንግሥት ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔን እየረዳ ነበር››
# የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የእርሱና የሕዝቡ ልብ ተናወጠ
በዚህ ወሬ ልባቸው መናወጡ ነፋስ ሲያናውጠው ከሚናወጥ ዛፍ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አካዝና ሕዝቡ በጣም ፈሩ››