# በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን ‹‹አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ዘመን›› — ይህ ታሪኩ የተፈጸመበት ነው፡፡ # ረአሶን… ፋቁሔ… ሮሜልዩ የሰዎች ስም # ረአሶንና… ፋቁሔ… ወጡ ነገሥታቱ የሚመሩት ሰራዊት እንደሆኑ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ረአሶንና… ፋቁሔ ከሰራዊታቸው ጋር ወጡ›› # ሊወጉ ወጡ ጸሐፊው፣ ከተማው ራሱ ውስጡ የሚኖሩ ሰዎች እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ›› # ለዳዊት ቤት ወሬ በደረሰ ጊዜ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዳዊት ቤት ወሬውን ሰሙ›› # የዳዊት ቤት ‹‹ቤት›› የሚለው ቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ቤተ ሰብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጉሥ አካዝና አማካሪዎቹ›› # ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል ‹‹ሶርያ›› እና፣ ‹‹ኤፍሬም›› ነገሥታቶቻቸውን ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ኤፍሬም›› መላው ሰሜናዊ የእስራኤልን መንግሥት ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔን እየረዳ ነበር›› # የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የእርሱና የሕዝቡ ልብ ተናወጠ በዚህ ወሬ ልባቸው መናወጡ ነፋስ ሲያናውጠው ከሚናወጥ ዛፍ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አካዝና ሕዝቡ በጣም ፈሩ››