am_tn/dan/05/22.md

1.5 KiB

ብልጣሶር

ይሄ ከአባቱ በመቀጠል ንጉስ የሆነው የናቡከደነፆር ልጅ ነው፡፡በትንቢተ ዳንኤል 5፡1 ላይ ይህንን ሥም እንዴት እንደፃፋችሁት ተመልከቱ፡፡

ልብህን አላዋረድክም

እዚህ ላይ“ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ወደራሱ ወደ ብልጣሶር ነው፡፡“ራስህን አላዋረድክም”

በሰማይ ጌታ ላይ ኮራህ

በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ልበ እርሱ ላይ እንደመኩራት ተቆጥሮ ተገልፆአል፡፡“በእግዚአብሔር ላይ አምፀሃል”

ከቤቱ

እዚህ ላይ “ቤቱ”ምንና የት እንደሆነ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በኢየሩሣሌም ውስጥ ከሚገኘው ቤተመቅደሱ”

ትንፍሽህን በእጁ የያዘው እግዚአብሔር

እዚህ ላይ “ትንፋሽ”የሚለው ቃል ሕይወትን የሚያመለክት ሲሆን “እጅ”የሚለው ቃል ደግሞ ሥልጣንን ወይም መግዛትን የሚያመለክት ነው፡፡“ትንፋሽ የሚሰጥህ እግዚአብሔር” ወይም“በሕይወትህ ላይ ሁሉ ገዢ የሆነው እግዚአብሔር”

መንገድህን ሁሉ

“የምታደርገውን ሁሉ”

ይህ ፅሕፈት ተፃፈ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይህንን መልዕክት ፃፈ”