# ብልጣሶር ይሄ ከአባቱ በመቀጠል ንጉስ የሆነው የናቡከደነፆር ልጅ ነው፡፡በትንቢተ ዳንኤል 5፡1 ላይ ይህንን ሥም እንዴት እንደፃፋችሁት ተመልከቱ፡፡ # ልብህን አላዋረድክም እዚህ ላይ“ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ወደራሱ ወደ ብልጣሶር ነው፡፡“ራስህን አላዋረድክም” # በሰማይ ጌታ ላይ ኮራህ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ልበ እርሱ ላይ እንደመኩራት ተቆጥሮ ተገልፆአል፡፡“በእግዚአብሔር ላይ አምፀሃል” # ከቤቱ እዚህ ላይ “ቤቱ”ምንና የት እንደሆነ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በኢየሩሣሌም ውስጥ ከሚገኘው ቤተመቅደሱ” # ትንፍሽህን በእጁ የያዘው እግዚአብሔር እዚህ ላይ “ትንፋሽ”የሚለው ቃል ሕይወትን የሚያመለክት ሲሆን “እጅ”የሚለው ቃል ደግሞ ሥልጣንን ወይም መግዛትን የሚያመለክት ነው፡፡“ትንፋሽ የሚሰጥህ እግዚአብሔር” ወይም“በሕይወትህ ላይ ሁሉ ገዢ የሆነው እግዚአብሔር” # መንገድህን ሁሉ “የምታደርገውን ሁሉ” # ይህ ፅሕፈት ተፃፈ ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይህንን መልዕክት ፃፈ”