am_tn/dan/05/22.md

28 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ብልጣሶር
ይሄ ከአባቱ በመቀጠል ንጉስ የሆነው የናቡከደነፆር ልጅ ነው፡፡በትንቢተ ዳንኤል 5፡1 ላይ ይህንን ሥም እንዴት እንደፃፋችሁት ተመልከቱ፡፡
# ልብህን አላዋረድክም
እዚህ ላይ“ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ወደራሱ ወደ ብልጣሶር ነው፡፡“ራስህን አላዋረድክም”
# በሰማይ ጌታ ላይ ኮራህ
በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ልበ እርሱ ላይ እንደመኩራት ተቆጥሮ ተገልፆአል፡፡“በእግዚአብሔር ላይ አምፀሃል”
# ከቤቱ
እዚህ ላይ “ቤቱ”ምንና የት እንደሆነ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በኢየሩሣሌም ውስጥ ከሚገኘው ቤተመቅደሱ”
# ትንፍሽህን በእጁ የያዘው እግዚአብሔር
እዚህ ላይ “ትንፋሽ”የሚለው ቃል ሕይወትን የሚያመለክት ሲሆን “እጅ”የሚለው ቃል ደግሞ ሥልጣንን ወይም መግዛትን የሚያመለክት ነው፡፡“ትንፋሽ የሚሰጥህ እግዚአብሔር” ወይም“በሕይወትህ ላይ ሁሉ ገዢ የሆነው እግዚአብሔር”
# መንገድህን ሁሉ
“የምታደርገውን ሁሉ”
# ይህ ፅሕፈት ተፃፈ
ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይህንን መልዕክት ፃፈ”