am_tw/bible/kt/holy.md

1.6 KiB

ቅዱስ፣ ቅድስና

“ቅዱስ” እና “ቅድስና” ኀጥእ ከሆነውና ፍጽምና ከሌለው ማንኛውም ነገር ፍጹም ልዩ የሚያደርገውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያመለክታል።

  • ፍጹም ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰዎችንም ሆነ ነገሮችን ቅዱስ ያደርጋል።
  • ቅዱስ ሰው የእግዚአብሔር ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር ለማምጣት ዓላማ ተለይቷል።
  • እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን የተናገረለት ነገር ማለት ለእርሱ መሥዋዕት እንዲቀርብበት መሠዊያ ለእርሱ ክብርና አገልግሎት ተለይቶአል።
  • እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ካላቀረባቸው በቀር ሰዎች ወደ እርሱ መቅረብ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሰዎች ኀጢአተኞችና ፍጽምና የጎደላቸው ናቸው።
  • በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለእርሱ ልዩ አገልግሎት ካህናትን ቅዱስ አድርጎ ይለይ ነበር። ወደ እርሱ መቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ሥርዐት በመፈጸም ከኀጢአት ነጽተዋል።
  • የእርሱ የሆኑትን ወይም ቤተ መቅደሱን የመሰሉ እርሱ ራሱን የገለጠበትን ቤተ መቅደሱን እንደመዳሰሉት አንዳንድ ቦታዎችንና ነገሮችን እግዚአብሔር ቅዱስ አድርጎ ለይቶአል።