am_tw/bible/kt/holy.md

11 lines
1.6 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ቅዱስ፣ ቅድስና
“ቅዱስ” እና “ቅድስና” ኀጥእ ከሆነውና ፍጽምና ከሌለው ማንኛውም ነገር ፍጹም ልዩ የሚያደርገውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያመለክታል።
* ፍጹም ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰዎችንም ሆነ ነገሮችን ቅዱስ ያደርጋል።
* ቅዱስ ሰው የእግዚአብሔር ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር ለማምጣት ዓላማ ተለይቷል።
* እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን የተናገረለት ነገር ማለት ለእርሱ መሥዋዕት እንዲቀርብበት መሠዊያ ለእርሱ ክብርና አገልግሎት ተለይቶአል።
* እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ካላቀረባቸው በቀር ሰዎች ወደ እርሱ መቅረብ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሰዎች ኀጢአተኞችና ፍጽምና የጎደላቸው ናቸው።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለእርሱ ልዩ አገልግሎት ካህናትን ቅዱስ አድርጎ ይለይ ነበር። ወደ እርሱ መቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ሥርዐት በመፈጸም ከኀጢአት ነጽተዋል።
* የእርሱ የሆኑትን ወይም ቤተ መቅደሱን የመሰሉ እርሱ ራሱን የገለጠበትን ቤተ መቅደሱን እንደመዳሰሉት አንዳንድ ቦታዎችንና ነገሮችን እግዚአብሔር ቅዱስ አድርጎ ለይቶአል።