# ቅዱስ፣ ቅድስና “ቅዱስ” እና “ቅድስና” ኀጥእ ከሆነውና ፍጽምና ከሌለው ማንኛውም ነገር ፍጹም ልዩ የሚያደርገውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያመለክታል። * ፍጹም ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰዎችንም ሆነ ነገሮችን ቅዱስ ያደርጋል። * ቅዱስ ሰው የእግዚአብሔር ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር ለማምጣት ዓላማ ተለይቷል። * እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን የተናገረለት ነገር ማለት ለእርሱ መሥዋዕት እንዲቀርብበት መሠዊያ ለእርሱ ክብርና አገልግሎት ተለይቶአል። * እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ካላቀረባቸው በቀር ሰዎች ወደ እርሱ መቅረብ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሰዎች ኀጢአተኞችና ፍጽምና የጎደላቸው ናቸው። * በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለእርሱ ልዩ አገልግሎት ካህናትን ቅዱስ አድርጎ ይለይ ነበር። ወደ እርሱ መቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ሥርዐት በመፈጸም ከኀጢአት ነጽተዋል። * የእርሱ የሆኑትን ወይም ቤተ መቅደሱን የመሰሉ እርሱ ራሱን የገለጠበትን ቤተ መቅደሱን እንደመዳሰሉት አንዳንድ ቦታዎችንና ነገሮችን እግዚአብሔር ቅዱስ አድርጎ ለይቶአል።