am_tw/bible/kt/highpriest.md

973 B

ሊቀ ካህን

“ሊቀ ካህን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተቀሩት እስራኤላውያን ካህናት መሪ በመሆን ለአንድ ዓመት እንዲያገለግል የተሾመ የተለየ ካህንን ያመለክታል።

  • ሊቀ ካህን የተለየ ኀላፊነቶች ነበር። በዓመት አንድ ጊዜ የሆነውን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ የሚፈቀድለት እርሱ ብቻ ነበር።
  • እስራኤላውያን ብዙ ካህናት ቢኖሯቸውም ለአንድ ዘመን አንድ ሊቀ ካህን ብቻ ነበራቸው።
  • ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህን ቀያፋ ነበር። የቀያፋ ሚስት አባት የነበረው የቀድሞው ሊቀ ካህንና ምናልባትም ከዚያ በኋላም በሕዝቡ ላይ ኀይልና ሥልጣን የነበረው ሐና አልፎ ይጠቀሳል።