# ሊቀ ካህን “ሊቀ ካህን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተቀሩት እስራኤላውያን ካህናት መሪ በመሆን ለአንድ ዓመት እንዲያገለግል የተሾመ የተለየ ካህንን ያመለክታል። * ሊቀ ካህን የተለየ ኀላፊነቶች ነበር። በዓመት አንድ ጊዜ የሆነውን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ የሚፈቀድለት እርሱ ብቻ ነበር። * እስራኤላውያን ብዙ ካህናት ቢኖሯቸውም ለአንድ ዘመን አንድ ሊቀ ካህን ብቻ ነበራቸው። * ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህን ቀያፋ ነበር። የቀያፋ ሚስት አባት የነበረው የቀድሞው ሊቀ ካህንና ምናልባትም ከዚያ በኋላም በሕዝቡ ላይ ኀይልና ሥልጣን የነበረው ሐና አልፎ ይጠቀሳል።