am_tw/bible/kt/highpriest.md

8 lines
973 B
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሊቀ ካህን
“ሊቀ ካህን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተቀሩት እስራኤላውያን ካህናት መሪ በመሆን ለአንድ ዓመት እንዲያገለግል የተሾመ የተለየ ካህንን ያመለክታል።
* ሊቀ ካህን የተለየ ኀላፊነቶች ነበር። በዓመት አንድ ጊዜ የሆነውን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ የሚፈቀድለት እርሱ ብቻ ነበር።
* እስራኤላውያን ብዙ ካህናት ቢኖሯቸውም ለአንድ ዘመን አንድ ሊቀ ካህን ብቻ ነበራቸው።
* ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህን ቀያፋ ነበር። የቀያፋ ሚስት አባት የነበረው የቀድሞው ሊቀ ካህንና ምናልባትም ከዚያ በኋላም በሕዝቡ ላይ ኀይልና ሥልጣን የነበረው ሐና አልፎ ይጠቀሳል።