am_tw/bible/kt/grace.md

8 lines
887 B
Markdown

# ጸጋ፣ ባለጸጋ
“ጸጋ” የሚለው ቃል ምንም ሳይለፋና ሳይደክም አንድን ሰው መርዳትን ወይም መባረክን ያመለክታል። “ባለ ጸጋ” ሌሎችን ጸጋ የሚያሳይን ሰው ይመለከታል።
* እግዚአብሔር ለኀጢአተኛ የሰው ልጆች ያለው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ስጦታ ነው።
* ጸጋ በደልና የሚጎዳ ነገር የፈጸመውን ሰው ይቅር ማለትንና ለእርሱ ደግ መሆንንም ያመለክታል።
* “ጸጋ ማግኘት” ከእግዚአብሔር ረድኤትና ምሕረትን መቀበልን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አንድን ሰው አስመልክቶ እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶ እነርሱን መርዳቱን የሚያመለክት ትርጕምንም ይጨምራል።