# ጸጋ፣ ባለጸጋ “ጸጋ” የሚለው ቃል ምንም ሳይለፋና ሳይደክም አንድን ሰው መርዳትን ወይም መባረክን ያመለክታል። “ባለ ጸጋ” ሌሎችን ጸጋ የሚያሳይን ሰው ይመለከታል። * እግዚአብሔር ለኀጢአተኛ የሰው ልጆች ያለው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ስጦታ ነው። * ጸጋ በደልና የሚጎዳ ነገር የፈጸመውን ሰው ይቅር ማለትንና ለእርሱ ደግ መሆንንም ያመለክታል። * “ጸጋ ማግኘት” ከእግዚአብሔር ረድኤትና ምሕረትን መቀበልን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አንድን ሰው አስመልክቶ እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶ እነርሱን መርዳቱን የሚያመለክት ትርጕምንም ይጨምራል።