am_tw/bible/kt/grace.md

887 B

ጸጋ፣ ባለጸጋ

“ጸጋ” የሚለው ቃል ምንም ሳይለፋና ሳይደክም አንድን ሰው መርዳትን ወይም መባረክን ያመለክታል። “ባለ ጸጋ” ሌሎችን ጸጋ የሚያሳይን ሰው ይመለከታል።

  • እግዚአብሔር ለኀጢአተኛ የሰው ልጆች ያለው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ስጦታ ነው።
  • ጸጋ በደልና የሚጎዳ ነገር የፈጸመውን ሰው ይቅር ማለትንና ለእርሱ ደግ መሆንንም ያመለክታል።
  • “ጸጋ ማግኘት” ከእግዚአብሔር ረድኤትና ምሕረትን መቀበልን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አንድን ሰው አስመልክቶ እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶ እነርሱን መርዳቱን የሚያመለክት ትርጕምንም ይጨምራል።