am_tw/bible/kt/good.md

1.6 KiB

መልካም፣ መልካምነት

“መልካም” የሚለው ቃል እንደ ምንባቡ ዐውድ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። እነዚህን የተለያዩ ቃሎች ለመተርጎም የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጕሞች ያቀርባሉ።

  • አጠቃላይ በሆነ መልኩ ከእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ዓላማና ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነገር መልካም ነው።
  • “መልካም” ነገር ደስ የሚያሰኝ፣ የላቀ ብልጫ ያለው፣ ሰዎችን የሚረዳ፣ ምቹ፣ ጠቃሚ ወይም ከግብረ ገብ አንጻር ትክክል ሊሆን ይችላል።
  • “መልካም” መሬት፣ “ለም” ወይም፣ “ፍሬያማ” ተብሎ ይጠራል።
  • “መልካም” ሰብል፣ ብዛት ያለው ሰብል ይባላል።
  • እንደ “መልካም ገበሬ” ሁሉ አንድ ሰው በሥራውና በሙያው ጠንቃቃና የተዋጣለት ከሆነ፣ “መልካም” ይባላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ”መልካም” አጠቃላይ ትርጕም “ከክፉ” ጋር በንጽጽR ነው የሚቀርበው።
  • “መልካምነት” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያማለክተው ግብረ ገባዊ ጥራትን ወይም በሐሳብና በተግባር ጻድቅ ሆኖ መገኘትን ነው።
  • የእግዚአብሔር መልካምነት መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን ለሰዎች በመስጠት እነርሱን መባረኩን ያመለክታል። ግብረ ገባዊ ፍጽምናውንም ሊያመለክት ይችላል።