# መልካም፣ መልካምነት “መልካም” የሚለው ቃል እንደ ምንባቡ ዐውድ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። እነዚህን የተለያዩ ቃሎች ለመተርጎም የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጕሞች ያቀርባሉ። * አጠቃላይ በሆነ መልኩ ከእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ዓላማና ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነገር መልካም ነው። * “መልካም” ነገር ደስ የሚያሰኝ፣ የላቀ ብልጫ ያለው፣ ሰዎችን የሚረዳ፣ ምቹ፣ ጠቃሚ ወይም ከግብረ ገብ አንጻር ትክክል ሊሆን ይችላል። * “መልካም” መሬት፣ “ለም” ወይም፣ “ፍሬያማ” ተብሎ ይጠራል። * “መልካም” ሰብል፣ ብዛት ያለው ሰብል ይባላል። * እንደ “መልካም ገበሬ” ሁሉ አንድ ሰው በሥራውና በሙያው ጠንቃቃና የተዋጣለት ከሆነ፣ “መልካም” ይባላል። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ”መልካም” አጠቃላይ ትርጕም “ከክፉ” ጋር በንጽጽR ነው የሚቀርበው። * “መልካምነት” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያማለክተው ግብረ ገባዊ ጥራትን ወይም በሐሳብና በተግባር ጻድቅ ሆኖ መገኘትን ነው። * የእግዚአብሔር መልካምነት መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን ለሰዎች በመስጠት እነርሱን መባረኩን ያመለክታል። ግብረ ገባዊ ፍጽምናውንም ሊያመለክት ይችላል።