am_tw/bible/kt/good.md

13 lines
1.6 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መልካም፣ መልካምነት
“መልካም” የሚለው ቃል እንደ ምንባቡ ዐውድ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። እነዚህን የተለያዩ ቃሎች ለመተርጎም የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጕሞች ያቀርባሉ።
* አጠቃላይ በሆነ መልኩ ከእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ዓላማና ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነገር መልካም ነው።
* “መልካም” ነገር ደስ የሚያሰኝ፣ የላቀ ብልጫ ያለው፣ ሰዎችን የሚረዳ፣ ምቹ፣ ጠቃሚ ወይም ከግብረ ገብ አንጻር ትክክል ሊሆን ይችላል።
* “መልካም” መሬት፣ “ለም” ወይም፣ “ፍሬያማ” ተብሎ ይጠራል።
* “መልካም” ሰብል፣ ብዛት ያለው ሰብል ይባላል።
* እንደ “መልካም ገበሬ” ሁሉ አንድ ሰው በሥራውና በሙያው ጠንቃቃና የተዋጣለት ከሆነ፣ “መልካም” ይባላል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ”መልካም” አጠቃላይ ትርጕም “ከክፉ” ጋር በንጽጽR ነው የሚቀርበው።
* “መልካምነት” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያማለክተው ግብረ ገባዊ ጥራትን ወይም በሐሳብና በተግባር ጻድቅ ሆኖ መገኘትን ነው።
* የእግዚአብሔር መልካምነት መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን ለሰዎች በመስጠት እነርሱን መባረኩን ያመለክታል። ግብረ ገባዊ ፍጽምናውንም ሊያመለክት ይችላል።